1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 4 2018

ዛሬ ከመቐለ ዓዲግራት የሚወስደውን ጎዳና የዘጉ የትግራይ ኃይሎች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ጎዳናው እንደዘጉ ነበሩ። ትላንት የግዚያዊ አስተዳደሩፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ የህወሓት ሊ/መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የሠራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች ከተቃዋሚዎቹ የሠራዊት አባላት ጋር ስላካሄዱት ዝግ ስብሰባየተባለ ነገር የለም።

የመቀሌ ከተማ
የመቀሌ ከተማ ምስል፦ Million Haileselassie/DW

የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ

This browser does not support the audio element.

የደሞዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ጥያቄ በመያዝ ትላንት በመቐለ የተቃውሞ ትእይንት ያደረጉት የትግራይ ሐይሎች የሰራዊት አባላት እስከ ማምሻው ድረስ መንገዶች ዘግተው የዋሉ ሲሆን፥ ይህ ተቃውሞ በሌሎች የትግራይ ሐይሎች አባላት ቀጥሎ ዛሬ ደግሞ ከመቐለ ቅርብ ርቀት ባለቸው አጉላዕ ጨምሮ በክልሉ ምስራቃዊ ዞን በርካታ ቦታዎች መንገድ በመዝጋት ቀጥሎ ውሏል። ይህ ተከትሎ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል፥ የህዝብ እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል። 

የትግራይ ሐይሎች አባላት ተቃውሞ

በተለይም በመቐለ ተቃውሞ ያደረጉት የትግራይ ሐይሎች ሰራዊት አባላት ትላንት ማምሻውን በሐወልቲ ሰማእታት አደራሽ ከክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከህወሓት መሪ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ይህ ውይይት ለሁሉም መገናኛ ብዙሐን የተከለከለ እና በዝግ የተደረገ ነው። የትግራይ ሐይሎችአባላቱ የደሞዝ ጭማሪ፣ ጥቅማጥቅሞች እንዲሁም ሌሎች ጥያቄዎች ማቅረባቸው ቀጥለዋል። እየቀጠለ ያለው ተቃውሞ ተከትሎ የድጋፍ መግለጫ ዛሬ ያወጣው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በበኩሉ፥ በትግራይ ያለው ስርዓት ለመገርሰስ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማሕበረሰብ ክፍሎች ጥያቄዎቻቸው ይዘው ተቃውሞው ይቀላቀሉ ሲል ጥሪ አቅርቧል። 

ፖለቲካዊ ቀውስ

በሌላ በኩል በትግራይ ስርዓቱ የፈጠረው ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቀውስ ተከስቶ ይገኛል ሲሉ የገለፁት የተቃዋሚው ትንሳኤ ስርዓት ቃንጪ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ደጋፊ ጎደፋይ በበኩላቸው የጦርነት እና የእርስበርስ ግጭት ስጋት እንዲሁም ስርዓት አልበኝነት መንገሱ እንደማሳያ ያነሱታል። 

በመቐለ ተቃውሞ ያደረጉት የትግራይ ሐይሎች ሠራዊት አባላት ትላንት ማምሻውን በሐወልቲ ሰማእታት አደራሽ ከክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከህወሓት መሪ ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይት ለሁሉም መገናኛ ብዙሐን የተከለከለ እና በዝግ የተደረገ ነው።ምስል፦ Million Haileselassie/DW

በዛሬው ዕለት ከመቐለ ዓዲግራት የሚወስደው ጎዳና የዘጉ የትግራይ ሐይሎችሰራዊት አባላት፥ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ጎዳናው እንደዘጉ ናቸው። ትላንት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጨምሮ ሌሎች የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች የተገኙበት እና ተቃውሞ ካደረጉ የሰራዊት አባላት ጋር በተደረገ ዝግ ስብሰባ ውጤት የተባለ ነገር የለም። 

የህወሓት ክስ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሳምንታዊ መልእክት በማለት ትላንት መግለጫ ያሰራጨው ህወሓት፥ የኢትዮጵያ መንግስት 'ከሃዲዎች' ብሎ በጠራቸው አካላት በመጠቀም ፀረ ትግራይ፣ ህወሓት እና የትግራይ ሐይሎች ፕሮፖጋንዳ እያካሄደ ይገኛል ሲል ከሷል። አሁንም ምርጫችን ሰላም ነው የሚለው የህወሓት መግለጫ፥ የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት የሚቃረን ተግባር ከመፈፀም ይቆጠብም ብሏል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ስምምነቱ በመጣስ እርስበርስ ይካሰሳሉ። 

በቀጠለው ፖለቲካዊ ቀውስ ላይ አስተያየት የሰጡን ፖለቲከኛው አቶ ደጋፊ ጎደፋይ በበኩላቸው የሰላም ስምምነቱ ይዘት በትክክል መተግበር ለበርካታ ቀውሶች መፍትሔ ሊሆን ይችላል ብለዋል።

ህወሓት ባቀረበው ክስ ዙርያ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ


 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW