1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቆዳ ውጤቶች ምርት ፈተና በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 1 2015

ከአፍሪካ ከፍተኛ የቁም አንስሳት ሃብት ያላት ኢትዮጵያ በዚህ የቆዳ ውጤቶች አምራችነት ከፍተኛ እድልና የተወዳዳሪነት አቅም እንዳላት ይነገራል። ይሁንና በተለያዩ ተግዳሮቶች ምክኒያት አገሪቱ በዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም አላገኘችም። ምክንያቱ “አንደኛውና መሰረታዊ ነገር ከብት እርባታው ለኢንደስትሪው የሚያመች አካሄድ የለዉም።“

Lederprodukte Messe in Addis Abeba Äthiopien
የቆዳ ውጤቶች ምርት ፈተና በኢትዮጵያምስል Seyoum Getu Hailu/DW

አንደኛውና መሰረታዊ ነገር ከብት እርባታው ለኢንደስትሪው የሚያመች አካሄድ የለዉም

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከቅዳሜ ሚያዚያ 28 ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዚህ የኢንደስትሪ ውጤት አውደ ርዕ ላይ በኢትዮጵያ በተለያዩ አይነት ምርት የተሰማሩ አምራቾችም እየተሳተፉ ነው፡፡ ከተሳታፊዎቹ አንዱ ደግሞ በኢትዮጵያ እምቅ አቅም አለው የሚባልለት የቆዳ እና ቆዳ ውጤቶች አምራቾች ይገኛሉ፡፡

የቆዳ ውጤቶች ምርት ፈተና በኢትዮጵያምስል Seyoum Getu Hailu/DW

በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾቹ በተለይም ከግብኣት አቅርቦትና የመንግስት ትኩረት ማጣት ጋር ተያይዙ ዘርፉ መድረስ ከሚገባው ስኬት በእጅጉ ያነሰ የማምረት ደረጃ ላይ እንዳለም ያነሳሉ፡፡ የቆዳ እጥረት በፋብሪካዎች ጎልቶ በሚነሳባት ኢትዮጵያ፤ በሌላ በኩል ግን ቆዳዎች ምንም ፈላጊ በማጣታቸው በየመንገዱ ሲጣሉ ነው የሚስተዋለው፡፡ የኢንደስትሪ ሚኒስቴርም ችግሩን ለምፍታት እልባት እያፈላለኩ ነው ይላል፡፡

በኢትዮጵያ የአምራች ኢንደስትሪ ዘርፉን ተግዳሮት ለመቅረፍ፣ የቅንጅት ስራዎችን በማሻሻል የኢንደስትሪ ዘርፎችን ተወዳዳሪ ለማድረግ ወጥኖ ቅዳሜ ሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተው የኢትዮጵያ ታምርት አውደ ርእይ (EXPO) በመካሄድ ላይ ነው፡፡ እስከ ግንቦት 02 ይቀጥላል የተባለው ይህ የአምራች ኢንደስትሪዎች አውደ ርዕይ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አምራች ኢንደስትሪዎች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ማስረዳት፣ ትስስሮችን መፍጠርና ችግሮቹን ነቅሶ ማውጣት በትኩረት የሚሰራበት መሆኑንም ከአዘጋጁ የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖምስል Seyoum Getu Hailu/DW

ዳልጋ የተሰኘው የቆዳ ውጤቶች አምራች ኩባንያ የቢዝነስ ማናጀር ወ/ሪት መዓዛ ገብረእግዚአብሄርን በዚህ አውደ ርዕይ ላይ አግኝተን ካነጋገርናቸው ናቸው፡፡ መሰል አውደ ርእይ ግብኣቶችን ለማግኘት ትስስር ለመፍጠር እንደሚረዳም አንስተዋል፡፡

አቶ እስማኤል በድሩ ደግሞ ዙምባ ማኑፋክቸር የተባለው ጫማዎችን አምርቶ ለውጪ ገበያ ብቻ የሚያቀርበውን ኩባንያ በስራ አስከያጅነት ይመራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ባሁን ወቅት ከዘርፉ መጠቀሟን በእጅጉ የሚጠራጠሩት አቶ እስማኤል፤ የጥሬ ቆዳዎች እጥረት አሁን ላይ ከአቅማቸው በታች እንዲሰሩ ከሚያስገድዳቸው ጉዳዮች ዋነኛው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ “ጥሬ ቆዳዎችን አዘጋጅተው ሚያቀርቡልን ፋብሪካቸዎች አንድም በምርት (በቆዳ) እጣረት በእጅጉ ፈተናሉ፡፡ ለስራው የሚረዳውን ኬሚካል አቅርቦት እንደሚፈትናቸውም እንሰማለን፡፡ ይህ ከስራ ቦታ ትበትና ከፋይናነስ ችግር ጋር ተዳምሮ ከአቅማችን በታች እንድናመርት ያስገድደናል፡፡”

የቆዳ ውጤቶች ምርት ፈተና በኢትዮጵያምስል Seyoum Getu Hailu/DW

አቶ ዓለምነው ገበየሁ ደግሞ ባቱ ታነሪ የተሰኘው የቆዳ አምራች ፋብሪካን ምርት ይዘው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ታድመዋል፡፡ ጥሬ ቆዳን ተቀብለው ለተለያዩ ምርቶች እንዲውሉ አድርገው በማምረት ለተለያዩ የቆዳ ውጤት አምራቾችም ያቀርባሉ፡፡ እሳቸውም ዘርፉን በእጅጉ የፈተነውን ተግዳሮች ሲያነሱ፤ “አሁን ላይ ለማምረት አንደኛው የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር አለ፡፡ ጥሬ እቃዎቹ በሚፈለገው ጥራትና መጠን ለፋብሪካዎቹ እየቀረቡ አደለም፡፡ ኬሚካሎችን ደግሞ ከውጪ ስለምናስገባ የውጪ ምንዛሪም በእጅጉ ስለሚፈትነን በሚፈለገው መጠን ማምረት አንችልም” ብለዋል፡፡

ከአፍሪካ ከፍተኛ የቁም አንስሳት ሃብት ያላት ኢትዮጵያ በዚህ የቆዳ ውጤቶች አምራችነት ከፍተኛ እድልና የተወዳዳሪነት አቅም እንዳላት የኢንደስትሪ ሚኒስቴርም ያነሳል፡፡ ይሁንና በተለያዩ ተግዳሮቶች ምክኒያት አገሪቱ በዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንዳላገኘችም እንዲሁ፡፡ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ናቸው፡፡ “አንደኛውና መሰረታዊ ነገር ከብት እርባታው ላይ በራሱ ለኢንደስትሪው የሚመች አካሄድ አይደለም የምንከተለው፡፡ ያ በራሱ ለቆዳ ኢንደስትሪው የሚፈለግ ጥራት የሚሟላ አልሆነም፡፡ የቆዳ አሰባሰብ ላይ ያለው ችግርም አለ፡፡ ዘርፉ የውጪ ግብዓትም ጥገኛ መሆኑ ካለብን የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንጻር ፈትኖናል፡፡ ይህ በተለይም ከኬሚካል ግዢ ጋር ተያያዘ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ የዘርፉን ችግር በጥናት ለምፍታት ትናት አጥንተናል በዚያው መሰረት የዘርፉን የግብዓት ችግር በመፍታት እና የፋይናንስ ችግሩን በመቅረፍ እንደ አገር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንስራለን” ሲሉ የዘርፉና ማነቆ እና መፍትሄ ያሉትን መልሰዋል፡፡

የቆዳ ውጤቶች ምርት ፈተና በኢትዮጵያምስል Seyoum Getu Hailu/DW

ለአምስት ቀናት በሚቆየው “የኢትዮጵያ ታምርት አውደ ርዕይ” ከቆዳ ውጤቶች በተጨማሪ ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ የተለያዩ የፋብሪካ ውጤቶች አምራች ኢንደስትሪዎችም ታድመውበታል፡፡

ስዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW