የበርሊን የቱሪዝም ትርዒት
ሐሙስ፣ የካቲት 29 2004ማስታወቂያ
በዓመቱ በዚሕ ሠሞን በርሊን-ጀርመን ዉስጥ ለጎብኚዎች የሚታየዉ ዓለም አቀፍ የሐገር ጎብኚዎች መስሕብ ትርዒት የዘንድሮዉ ትናንት በይፋ ተከፍቷል።ዘንድሮ ለ46ኛ ጊዜ በተከፈተዉ ትርዒት ላይ አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ሐገራትን የወከሉ ከአስር ሺሕ ስድስት መቶ የሚበልጡ ድርጅቶችና ኩባንዮች ተካፋዮች ናቸዉ።የዘንድሮዉ ትርዒት የተከፈተዉ የሐገር ጎብኚዎች እንቅስቃሴ በተለያዩ ምክንያቶች በታጎለበት ወቅት ነዉ።ታዛቢዎች እንደሚሉት የአዉሮጳ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት፥ የአረብ ሐገራት አብዮት፥ የተፈጥሮ መቅሰፍት፥ እና በኢትዮጵያ ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ሐገር ጎብኚዎች መገደልና መታገታቸዉ «ጢስ አልባ ኢንዱስትሪ» የሚባለዉን መስክ ጎድቶታል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ይልማ ሐይለ ሚካኤ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ