የበኒሻንጉል ግጭት
ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2012
ማስታወቂያ
በኒ ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ግልገል በለስ በተባለዉ ከተማ ባለፈዉ ሳምንት አርብ የተቀሰቀሰዉ ግጭት የጎሳ መልክና ባሕሪ ተላብሶ ወደተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች መዛመቱን ነዋሪዎቹ አስታወቁ።ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በአካባቢዉ የሰፈረዉ ፀጥታ አስከባሪ ኃይል እስካሁን ግጭቱን ማስቆም አልቻለም ወይም አልፈለገም።ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በግጭቱ በትንሽ ግምት 8 ሰዉ ተገድሏል።የበኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽነር መሐመድ አምደኒል ግን ፖሊስ የደረሰዉን ጉዳት መጠን ገና «እያጣራ ነዉ።» ይላሉ።
ነጋሳ ደሳለኝ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ