1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበኒ ሻንጉል መስተዳድርና የባለሐብቶች መሬት 

ረቡዕ፣ የካቲት 11 2012

የበኒ ሻንል ጉሙዝ ክልላዊ መስተዳድር፣ ከመስተዳድሩ የተረከቡትን መሬት በአግባቡ አላለሙም ካላቸዉ ባለሐብቶች ላይ የወሰደዉን መሬት ለስራ አጥ ወጣቶች ማሕበራት ማደሉን አስታወቀ። የክልሉ የመሬት አስተዳደር ቢሮ እንዳስታወቀዉ በክልሉ እጣን ለማምረት ተፈቅዶላቸዉ መሬት የተረከቡ 16 ባለሐብቶች በተረከቡት መሬት በአግባቡ አልሰሩበትም።

Äthiopien Ahemde Rama
ምስል DW/N. Dessalegn

56 የእርሻ ትራክተሮችና 26 ፒክ አፕ መኪኖች መወረሳቸው ተገልጧል

This browser does not support the audio element.

የበኒ ሻንል ጉሙዝ ክልላዊ መስተዳድር፣ እጣን ለማምረት ተፈቅዶላቸዉ መሬት የተረከቡ 16 ባለሐብቶች በተረከቡት መሬት በአግባቡ አልሠሩም በሚል መሬቱ  በ35 ማሕበራት ለተደራጁ 500 ወጣቶች መዛወሩን አንድ የመሬት አስተዳደር ኃላፊ አስታዉቀዋል። ኃላፊዉ እንደሚሉት እዚያዉ በኒ ሻንጉል ክልል የግል ባለሐብቶች ከቀረጥ ነፃ ከዉጪ አስገቧቸዉ የተባሉ 56 የእርሻ ትራክተሮችና 26 ፒክ አፕ መኪኖች ተሰዉረዋል።

በበኒ ሻንል ጉሙዝ ክልል የአካባቢ መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ የገጠር መሬት አስተዳደርና እና አጠቃቀም የስራ ሂዴት አስተባባሪ  አቶ አህመድ ራማ ለዲ ዳቢለው እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ በክልሉ 711 ባለሀብቶች በእርሻ ኢንቨስትመንት፣በእጣን ምርት እንዲሁም በማዕድን ዘርፍ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል 20 ባለሀብቶች   በእጣን ምርት የተሰማሩ ሲሆን 16ቱ በወሰዱት መሬት ላይ በአግባቡ  ባለማልማታቸው ከዚህ ቀደም  የክልሉ የኢንቨስትመንት ቦርድ ውሰኔ መሰረት ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ተደርጎ መሬቱን ለክልሉ ስራ አጥ ወጣቶች ተላልፎ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ሶስት ዞኖች የተደረጁ 35 ማህበራት እና አምስት መቶ(500) የሚደርሱ ወጣቶች በእጣን ምረት ስራ እንዲሳተፉ መደረጉን ጠቁመዋል።

ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ለመግባት ፈቃድ በወሰዱ ባለሀብቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር ገብተው ለታለመለት ዓላማ ያልዋሉ  የ37 ባለሀብቶች ንብረት የሆኑ 56 የእርሻ ትራክተሮችና 26 ፒክ አፕ መኪኖች ደግሞ የት እንደገቡ አይታወቅም ብለዋል፡፡ ንብረቶቹ ባሉበት እዲታገዱና የገቢዎች ሚኒስቴር ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ከዚህ ቀደም ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ክትትል እየተረደረገም ነው ብለዋል፡፡ በክልሉ የተሰማሩ ባለ ሀብቶች አብዛኖቹ ለአርሶ አደሩ የቴክሎጅ ሽግግር ማድረግ አልቻሉም ያሉት አቶ አህመድ ከዚህ ቀደም በማዕድን ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ይሰጥ የነበረው 300 ሄክታር መሬት ተቀንሶ 20 ሄክታር ብቻ እንዲሰጣቸው መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንቨስትመንት ቦርድ ባለፈው ዓመት ታህሳስ መጀመሪያ 2011 ዓ.ም  ላይ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በክልሉ የተለያዩ ስፍራዎች ከ62ሺ ሔክታር  በላይ የኢንቨስትመንት  እርሻ  መሬት ወስደው ወደ ስራ ያልገቡና ያላለሙ የተባሉ አንድ መቶ ሁለት (102) ባለሀብቶች ፈቃዳቸው ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ   መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡በመተከል  ዞን ጉባ፣ ከካማሺ ያሶ እና ከአሶሳ ዞን ኩሙሩክ  የተባሉ ወረዳዎች  ደግሞ በክልሉ ለኢንቨስትመንት  የተመረጡ አካባቢዎች ናቸው፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW