1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የበአል ጥቅል አገልግሎት

እሑድ፣ ሚያዝያ 16 2014

ለዝቅተኛው የሕብረተሰብ ክፍልና ለበጎ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅሎች እንዳሉም እንዲህ አጫውተውናል። ድርጅቱ ለሙስሊሞች የአፍጥር ፕሮግራም የሚሆኑ አግልግሎቶችም እየሰጠ ነው።

ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የበአል ጥቅል የገበያ አገልግሎት

This browser does not support the audio element.

ሐበሻ የምግብ ቤት ለቤት አዳይ ድርጅት  የዛሬ ሁለት አመት ስራ የጀመረው በኮረና ወረርሺኝ ምክንያት በነበረው ቤት የመዋል ግዴታ ወቅት እንደሆነ የድርጅቱ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙዲን አብዲሻ ገልጾልናል። በአሁኑ ጊዜ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ለአመት በአል ለእzn enaለአፍጥር የሚያስፈልጉ ምግቦችና አስፈላጊ ግብአቶችን ቤት ለቤት እንደሚያድል አጫውተውናል። ለፋሲካ በአልም የተለያዩ የአመት በአል ጥቅል አገልግሎቶች እየሰጠ እንደሆን አቶ ሳሙዲን ገልጸውልናል።
ከአስር እስከ አስራ ሰባት ሺ ብር የሚጠይቀው አገልግሎት በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የሕብረተሰብ ክፍል ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር አይክብድም አሁን ካለው ተጨባጭ የገበያ ዋጋ ሲነጻጸር የነሱ የተሻለና ሁሉንም በአንዴ የሚያቀርብ መሆኑን አብራርተዋል።

ድርጅቱ ለሙስሊሞች የአፍጥር ፕሮግራም የሚሆኑ አግልግሎቶችም እየሰጠ እንደሆነ አቶ ሳሙዲን ገልጸውልናል።  

ምስል፦ Seyoum Getu/DW


ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር 

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW