1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበዓል ሸመታ በአዲስ አበባ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 6 2015

አንድ ኪሎ ግራም ቅቤ 700 ብር፣ አይብ እንደየደረጃው ከ200 እስከ 250 እንዲሁም እንቁላል 12 ብር እንደሚሸጥም ሻጭና ሸማቹ ይሸማመታሉና ይህነ ተገንዝበናል፡፡አንድ ኪሎ ሽንኩር እስከ 40 ብር የሚሸጥ ሲሆን ይህም ካለፉት በዓላት ጭማሬ መኖሩን ማረጋገጫ ነው፡፡ ዶሮ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ከ350 እስከ 800 ብር እየተሸጠም ነው

Äthiopien Addis Abeba | Ostermarkt
ምስል Seyoum Getu/DW

የበዓል ገበያ በአዲስ አበባ

This browser does not support the audio element.

           
የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዛሬ የስቅለት በዓልን እያከበሩ ነዉ።ከነገ ወዲያ ዕሁድ ደግሞ ፋሲካ ይከበራል።በዓሉን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባ ዉስጥ እንደተጠበቀዉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አሻቅቧል።የሕብረት ሥራ ማሕበራት ገበያዉን ያረጋጋል ያሏቸዉን ሸቀጦች እያቀረቡ ቢሆንም ዋጋዉ ከነዋሪዉ አቅም ጋር የሚጣጣም ዓይነት አይደለም።
ለበዓሉ ግብይት ድምቀትን ከሚያስተናግዱ ስፍራዎች  መሃል አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጎን የሚገኘው የኤግዚቢዥን ማዕከል እንደወቀትሮው በዓል መዳረሻ በርካታ ገቢያተኞችን አገናኝቶአል፡፡ 
ከዚህ ስፍራ በተጨማሪ በመዲናዋ በዓልን በምግብ ፍጆታ አቅራቢነታቸው የሚያደምቁ ሌሎችም የግብዓት አቅራቢ ስፍራዎች አሉና፤ በተለምዶ ጀሞ ወደ ሚባል ስፍራ በማምራት ከእንስሳት እስከ የቤት ውስጥ መሰረታዊ ፍጆታ ወደ ሚያቀርብ የህብረት ስራ ማህበር አመራን፡፡ 
መሰረት በቀለ እንደ ቅቤ እና አይብ ያሉ እንደ እንቁላል ያሉት የእንስሳት ተዋጥኦዎችን እና ሌሎችም የበዓል ማድመቂያ ግብዓቶችን እየሸጠች ነው ያገኘናት፡፡ አንድ ኪሎ ግራም ቅቤ 700 ብር፣ አይብ እንደየደረጃው ከ200 እስከ 250 እንዲሁም እንቁላል 12 ብር እንደሚሸጥም ሻጭና ሸማቹ ይሸማመታሉና ይህነ ተገንዝበናል፡፡ 
ዮሃንስ መኮንን ደግሞ ጨፌ የተባለ የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ ስራ አስከያጅ ናቸው፡፡ ከበሬ እና ፍየል እስከ ሽንኩርትና ዶሮ ብሎም ሌሎች የቤት ውስጥ ፍጆታ ግብዓቶችን በማህበሩ በገፍ ለበዓል መቅረቡን በማስረዳትም ህብረታቸው ከትርፋማነትም በላይ ገቢያን የማረጋጋት ዓለማን አንግቦ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡
በዚህ አንድ መካከለኛ እና በመጠን ከፍ ያለ በሬ ከ40 እስከ 60 ሺህ ብር ተቆርጦለት አስተውለናል፡፡ አነስተኛ እና መካከለኛ የጠቦትነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ፍየሎች ደግሞ ከ2 ሺህ 500 እስከ 5 ሺህ 500 ብር እንደዲሸጡ ዋጋ ተቆርጦ ገቢያተኛው በሸመታ ላይ መሆኑንም አስተውለናል፡፡የትንሳኤ በዓል ግብይት በአዲስ አበባ
በዚህ ስፍራ አንድ ኪሎ ሽንኩር እስከ 40 ብር የሚሸጥ ሲሆን ይህም ካለፉት በዓላት ጭማሬ መኖሩን ማረጋገጫ ነው፡፡ ዶሮ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ከ350 እስከ 800 ብር እየተሸጠም ነው፡፡
በቅርቡ በኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ሳይጠበቅ አስር ሺህ መግባቱን ተከትሎ መንግስት ምርትን በተለይም በህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች አማካይነት በገፍ ወደ ከተማ ለማስገባት መጣሩን ደጋግሞ ያነሳል፡፡ በዚህ በጎበኘነው የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ አንድ ኩንታል ጤፍ አንደኛ ደረጃ ከሆነ 6 ሺህ 900 ብር ይሸጣልም ተብሏል፡፡ 
በዚህ አከባቢ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የስራ ኢንተርፕራይዝ ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድልአየሁ ታምሬ፤ ገቢያን ለማረጋጋት እንደ ዋና መሳሪያ መንግስት እየተጠቀመ የሚገኘው አቅርቦትን ማሻሻል ላይ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህም ሆን ዘንድ ምርት በቅናሽ በህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት የሚቀርብባቸው ስፍራዎች በየአከባቢዎቹ መበራከታቸውን አመልክተዋል፡፡
አቶ አምባዬ ወልዴ ደግሞ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው፡፡ “አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ላይ ብቻ ወደ 138 ሁለገብ የህብረት ስራ ማህበራት በኛ ስር ብቻ አሉ፡፡ የግብርና፣ የኢንደስትሪ እና የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የማዳረስ ስራ በነዚህ ማህበራት በመስራት ገቢያን የማረጋጋት ስራ ከናወናል፡፡ ገቢያ በርግጥ በዘላቂነት የሚረጋጋው በአቅርቦት ላይ ተግቶ በመስራት በመሆኑ እሱ አስፈላጊ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ገቢያው እንዳይረጋጋ በሚደረግ መጠን የምርት እጥረት ባለመኖሩ ምርቶች በህብረት ስራ ማህበራቱ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡”በአዲስ አበባ የበግ፣ ፍየል እና ሠንጋ ዋጋ እጅግ አሻቅቧል
በኢትዮጵያ በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ የመጣው የምርት ዋጋ ነዋሪዎችን ክፉኛ ማማረሩ ደጋግሞ ተስተውሏል፡፡ 

የበዓል ገበያ በአዲስ አበባ-ፍየልና በሬ ምስል Seyoum Getu/DW
የዶሮ አቅርቦት ለአዲስ አበባ ሸማችምስል Seyoum Getu/DW

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW