የበዓል አከባበር ግጭት በተስተዋለባቸው የኦሮሚያ አከባቢዎች
ሐሙስ፣ መስከረም 1 2018
በኦሮሚያ ክልል በተሌዩ አቅጣጫዎች ያለፉትን ጥቂት ዓመታት በግጭት ውስጥ ያለፉ አከባቢዎች ለነዋሪዎቹ ብርቱ ፈተናን ደቅኗል።በአውዳመት የወትሮው ሙላት የጎደለባቸው በነዚህ አከባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ አካላት ዛሬ አንድ ተብሎ በተጀመረው አዲሱ ዓመት እንደ ሰላም የሚሹት አንዳችም ነገር የለም፡፡
አየለ የተባሉት የምዕራብ ወለጋ ዞንባቦጋምቤል ወረዳ ተፈናቃይ ከዛሬ አምስት ዓመታት በፊት እንደ ዛሬዋ ለት ያለውን የዘመን መለወጫ እለትን የሚከብሩት በተለየ ድባብ በአብሮነትና ከፍ ባለም የፍቅር ስሜት ነበር፡፡ የቀድሞ ቤተሰብ አስተዳዳሪ የአሁኑ ተፈናቃይ አቶ አየለ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየታቸውም የዛሬን አያደርገው የሚል የቁጭት አስተያየታቸው ይህንኑን ያጎላል፡፡ “በቤታችን ሙክቱን አርደን ማርና ወተተቱን አዘጋጅተን በደስታ በሙሉ ቤት በአብሮነት ነበር አውዳመቱን የምናሳልፈው፡፡ ያ ዛሬ ላይ ግን ባጣም ርቆን ሽሮ እንኳን በዚህ ለት ናፍቆናል” ሲሉ ነው አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡
እናም ይላሉ ላለፉት አምስት ኣመታት የተፈናቃይ ኑሮን እየገፉ ያሉት አየለ፤ “በአዲሱ ዓመት ባለቀዬ ሆነን ከተረጂነት ወጥተን ወጥተን ወርደን በመስራት የምናፈራው የስራ ውጤታችን መብላት፤ ለወግማዕረግ የምናበቃቸው ልጆቻችንን ለትምህርት ቤት ማብቃት” ከዋነኞቹ ምኖታቸው መሆኑን አስረዱ፡፡ በአዲሱ ዓመት ካለፉት አምሰርት ዓመታት የፈተና ጊዜ በተሻለ አዲስ ለውጥን የሚመኙት አስተያየት ሰጪው ከጠባብ የተፈናቃዮች ሸራ በመውጣት በለመዱትን ቀዬያቸው ዳግም መኖር ያምታልን ሲሉም ምኞታቸውን ገለጹ፡፡
ከማል የተባሉ ሌላው አስተያየት ሰጪ የኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞንደራ ወረዳ የሰላሌ ነዋሪ፤ “አዲሱ ዓመት ችግር ጠፍቶ ሃብት፣ መገዳደል ጠፍቶ ፍቅር፣ አለማወቅ በእውቀት የሚተካበት፣ መሸነፍ ጠፍቶ ማሸነፍ የሚመጣበት፣ መከፋፈል ጠፍቶ አንድነት የሚሰፍንበት፣ በመግባባት ሰላም መንገድ የምንሻበት እንዲሆን ነው የምንፈልገው” ይላሉ፡፡ ባለፉት ዓመታት ያጣነው ነገር አለ የሚሉት አስተያየት ሰጪው የሰላሌ ነዋሪ በቅርቡ ተጠናቆ ደስታን ያጎናጸፈን ካሉት የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንኳ አንድነትን ዋጋ መገንዘብ ይቻላል ሲሉ ነው ሃሳባቸውን ያጋሩን፡፡
ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ነው፡፡ በዚህም አከባቢ ባለፉት ሶስት አራት ዓመታት ህዝብን ዋጋ አስከፍሏል ያሉት የሰላም እጦት ችግር በአዲሱ ዓመት ይቀረፍ ይሆን የሚሉት በጉጉት የሚጠብቁት ዋናው ጉዳይ ነው፡፡ “በአዲሱ ዓመት የምትመበኘው ሶስት ነገሮች ብባል ሰላም፣ ሰላም እና ሰለም እላለሁ” በማለት የጠፋው ሰላም ዋጋን ያጎሉት አስተያየት ሰጪው፤ ያለፉትን ዓመታት ህዝቡ የከፈለው ዋጋ እጅግ ከባድ መሆኑን በማስረዳት በዚህ በአዲስ መንፈስ በተያዘው ዓመት ተፋላሚዎች ቀልብ በመግዛትየሰላምን አማራጭ ብቸኛው መንገድእንዲያደርጉ ላቸውን ምኞች ገልጸዋል፡፡
በሌላው የክልሉ አቅጣጫ ከደቡብ ኦሮሚያ የጉጂና ምስራቅ ቦረና አዋሳኝ ወረዳ አስተያየታቸውን የሰጡን ነዋሪ፤ “ያለፉት ጢቂት ዓመታት በጉጂ ዘንድ በደስታ ሳይሆን በብዙው በሀዘንና በአሉታዊ የሚገለጽ ነው፡፡ የአዲሱ ዓመት ምኞታችን ይህ እንዲቀየርልን ነው፡፡ በተለይ ባለፉት ሁለት ኣመታት በዞኑ በመጣ አዲስ መዋቅር አስከፊ አለመረጋጋትን አሳልፈን ያለእልባት በዚያው መንገድ እየተጓዝን ነው፡፡ በአዲሱ ዓመት ይህ ችግር አልፎ ልክ በቅርቡ እንደተሳካው የታላቁ ህዳሴ ግድብ በሁሉ የተሳካ ዓመት ሁንልን የሚል ሃሳብ ነው ያለን” ሲሉ ነው ሀሳባቸውን ያጋሩን፡፡
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ