1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የበይነመረቡ ትእይንተ-ህዝብ የሰላም ጥሪና የተሰጡ አስተያየቶች

ሥዩም ጌቱ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 3 2017

ከሰሞኑ ከብሔራዊው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፊናቸው ኢትዮጵያ ውስት ስለሰላም የሚጣራው ጦርነት አጥማቂው እራሱ ነው የሚል ትችት በመሰንዘር መንግስታቸው ግን ከየትኛውም ወገን ጋር ሰላም ማውረድ እንደሚሻ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ባለፈዉ ቅዳሜ በበይነ-መረብ የተደረገዉን ትዕይተ-ሕዝብ፣ ዉይይትና  የሠላም ጥሪን ካስተባበሩት አንዱ አንጋፋዉ ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌዉ
ባለፈዉ ቅዳሜ በበይነ-መረብ የተደረገዉን ትዕይተ-ሕዝብ፣ ዉይይትና የሠላም ጥሪን ካስተባበሩት አንዱ አንጋፋዉ ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌዉምስል፦ privat

የበይነመረቡ ትዕይንተ-ህዝብ የሰላም ጥሪና የተሰጡ አስተያየቶች

This browser does not support the audio element.

 

ከሰሞኑበኢትዮጵያ ጉዳይ እንመክራለን ባሉ ስለኢትዮጵያ ይመለከተናል ያሉ የተለያዩ የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ የሚገኙ ልሒቃን የመሩት የበይነ መረብ ትእይንተህዝብ ሲካሄድ በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆምና ሰላም እንዲሰፍን የሚሉ ድምፆች ጎልተው ተስምተዋል፡፡

በበይነ መረቡ ሰልፍ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህምድን አስተዳደር የተቹ ተሳታፊዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ መቋጫ ያጣው ግጭት ድርድር ላይ በተመሰረተ መንገድ እንዲወገድ የሚል ሃሳብንም አስተጋብተዋል፡፡

ከሰሞኑ ከብሔራዊው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፊናቸው ኢትዮጵያ ውስት ስለሰላም የሚጣራው ጦርነት አጥማቂው እራሱ ነው የሚል ትችት በመሰንዘር መንግስታቸው ግን ከየትኛውም ወገን ጋር ሰላም ማውረድ እንደሚሻ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬሌ የሰጡ ተንታኝ በፊናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ቀዳሚው ነገር ማህበረሰባዊ ለውጥ ላይ መስራት ነው ብለዋል፡፡

የበይነመረቡ ትእይንተህዝብ አላማ

በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊመንገድ የሚታገለውን የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲን በምክትል ሰብሳቢነት የሚመሩት ፖለቲከኛ ራሔል ባፌ (ዶ/ር) በቅዳሜ ምሽቱ የበይነመረቡ ትእይንተህዝብ ቀጥተኛ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል ሲሆኑ የመድረኩን ዓለማ በተመለከተ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ አጋርተዋል፡፡ “ለኔ ህዝባችንም ማስተዋል ያለበት የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ሊኖር ይችላል” ያሉት ፖለቲከኛዋ የበይነመረቡ ትዕይንተህዝብ ዋና ዓለማ ሰላምን መስፈን የጠየቀ ሲሆን ግቡም እንደ አገር ያለን አጀንዳ አንድ ላይ ማምጣት ነው ብለዋል፡፡ መድረኩ አካታች ነበር ያሉት ዶ/ር ራሔል “አስተማሪም ነበር” ብለውታል፡፡

በበይነመረቡ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ያለው ጥርጣሬ

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ያጋሩት ለዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያገለገሉት የዓለማቀፍ ህግ ባለሙያና የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉት አቶ ባይሳ ዋቅዎያ ግን ሰሞነኛውን የበይነመረብ ትዕንተህዝብ ስካታማነትን በጥርጣሬ ነው የተመለከቱት፡፡ “ተሰብስበው ሰላም ይስፈን በሰላም ብቻ መቋጨት አለበት እንደራጅ የተባለው” በህዝቡ ዘንድ ሊያገኝ የሚችለውን ቅቡልነት በጥያቄ ያነሱት አቶ ባይሳ ትልቁ እልባት ሊህቃኑ ህዝቦችን በአንድነት የሚኖራቸውን አጀንዳ በመንደፍ እንጂ ህዝብን ህዝብ ላይ በማነሳሳትና መጠቀሚያ በማድረግ ተፈላጊው ሰላም መምጣት ስለመቻሉ ጥርጣሬያቸው ይጎላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሰላም የሚጣራው «ጦርነት ጠማቂው እራሱ ነው» የሚል ትችት በመሰንዘር መንግስታቸው ግን ከየትኛውም ወገን ጋር ሰላም ማውረድ እንደሚሻ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ምስል፦ Fana Broadcasting Corporate S.C.

ይልቅ “የቤት ስራው ከባድ ነው” የሚሉት አቶ ባይሳ ከባለፉት ጢቂት ዓመታት አሁን ላይ በሊህቃኑ ህዝብ መሃል የተፈጠረው ቁርሾ ልሽር የሚችለው ችግሩን የፈጠሩ አካላት ከመድረኩ ገለል ሲሉ ነው በማለት አስተያየታቸውን አክለዋልም፡፡ ሰላም ማምጣቱ “አይቻልም አይደለም” ያሉት አቶ ባይሳ ነገር “የሃይማኖት ተቋማትን ከማጣጣል እስከ ብሔርን በብሔር ላይ ማነሳሳት” የሰሩ አካላት ሰላምን ያመጣሉ የሚል እምነታቸው የተሟጠጠም እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ መፍትሄውስ ከየት ይምጣ የተባሉት የዓለማቀፍ ህግ ባለሙያና ተንታኙ፤ ሊህቃን የፈጠሩትን ስህተት አምነው ማህበረሰቡን በማንቃት በረጅም ሂደት ምናልባት ተፈላጊው መተማመንና ሰላም ሊያሰርጹ እንደሚቻልም ተስፋው መኖሩንም አንስተዋል፡፡

 የኢትዮጵያ ግጭትና የሰላም ፍላጎት የመንግስት እይታ

ከሰሞኑ ከብሔራዊው የኢትዮጵያቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ በኃይል ፍላጎትን የማሳካት ዝባሌዎች ዋናው መንስኤው የሊህቃን ሽኩቻ መሆኑን በመግለጽ፤ የግጭቶች መበራከትም ከዚሁ እንደሚነሳ በአስተያየታቸው ጠቁመዋል፡፡ “ስልጣን ስልጣን የሚሆነው እኔ ከያዝኩት ብቻ ነው፤ እኔ ከያዝኩት ትክክል ካልሆነ የተበላሸ ነው” ብለው የሚያስቡ መኖራቸውን ያመለከቱት ዐቢይ፤ እነዚህ እሳቤዎች በሚበራከቱበት ስፍራ ግጭቶቹ ይበራከታሉ ነው ያሉት፡፡

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚሁ ጋር አያይዘው በሰጡት ማብራሪያቸው “ክላሽ አንጋችና ጦርነት ጠማቂ” ብለው የጠሩት አካል ስሸነፍ ከሳሽና የሰላም ፈላጊ ሆኖ ራሱን ያቀርባል በማለትም ትችት ሰንዝረዋል፡፡ መንግስታቸው ስለሰላም ያለው እሳቤ ግልጽ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነትን በማሳያነት አቅርበው ከሁሉም ተፋላሚዎቻቸው ጋር ሰላም ማውረድን እንደሚሹም ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡    

ሥዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW