1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቡለኑ ጥቃት እና የስጋት ዳመና ያጠላበት የመተከል የጸጥታ ኹኔታ

ሰኞ፣ ኅዳር 15 2018

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ ማለዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ተናገሩ።

የመተከል ዞን
የአካባባው ነዋሪ መሆናቸውን የሚናገሩት የአይን ምስክር እንደሚሉት የቅዳሜ ማለዳውን በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ጉዳት በኢትዮጵያመንግስት በሚደገፉ ሚሊሻዎች እና በኦሮሞ ታጣቂ ቡድን መካከል የተፈጠረ የተኩስ ልውውጥን ተከትሎ የመጣ ነው ይላሉ ።

የቡለኑ ጥቃት እና የስጋት ዳመና ያጠላበት የመተከል የጸጥታ ኹኔታ

This browser does not support the audio element.

በቡለን ወረዳ የደረሰው ጥቃት 

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ ማለዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ተናገሩ። የቡለን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በፌስ ቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ በወረዳዋ ባኩጂ ቀበሌ «ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድን »  በንጹኃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጥቃት አድርሷል ሲል ከሷል። የቡለን ወረዳን ጨምሮ በመተከል ዞን በበርካታ ቀበሌዎች አሁንም የጸጥታ ስጋት መኖሩን ዶቼ ቬለ ካነጋገራቸው ነዋሪዎች ተረድቷል።

ከዓመታት ግጭት እና ጥቃት አንጻራዊ ሰላም እና መረጋጋት እያሳየች ነው ሲባልላልት የሰነበተችው መተከልባለፈው ቅዳሜ ማለዳ የተሰማው አሰቃቂ ዜና መረጋጋቱን የሚሸረሽር፣ ለነዋሪዉ ሌላ የጸጥታ ስጋት ሆኖ ዳግም ተከስቷል። የቡለን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ትናንት እሁድ በፌስ ቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ በባኩጅ ቀበሌ ጸንፈኛ ታጣቂ ቡድን ህዳር 13/2018 ዓ/ም ከንጋት 11:30 በመግባት በንጹሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጥቃት ማድረሱን የወረዳዋ ምክትል አስተዳደሪ አቶ ሺበሺ ባሬዳ መናገራቸውን ዘግቧል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁን የወረዳዋ ተመራጭ የህዝብ ተወካይ በጥቃቱ ከሰላሳ በላይ ንጹሃን መገደላቸውን አረጋግጠዋል። 


« ሰሞኑን ቅዳሜ ሌሊት 11 ሰዓት ላይ ቡለን ወረዳ ባኩጂ ቀበሌ ላይ ነው እንግዲህ ከተማ ገብተው ንጹኃን ላይ ጭፍጨፋ ያደረጉት ሰው እየተኛ ባለበት እና ገና እየነቃ ባለበት ንጋት ላይ ማለት ነው ያገኙትን በሙሉ ጥቃት ፈጽመው ከ30 በላይ ንጹኃን እንደሞቱ ነው ያለን መረጃ »
የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጥቃት አድራሹን «ጽንፈኛ ቡድን » ከማለት ባሻገርየትኛው ቡድን እንደሆነለይቶ አልገለጸም። ነገር ግን የህዝብ ተወካዩ  መንግስት «ሸኔ» ብሎ የሚጠራው ቡድንን ተጠያቂ ያደርጋሉ ። በጥቃቱ ከተገ,ደሉት ባሻገር በርካቶች መጎዳታቸውንም ይገልጻሉ።
«የቆሰሉም አሉ ፤ ሆስፒታልም የገቡ ፤ ከቆሰሉት ውስጥም ህይወታቸው ያለፈ አሉ። ከጥቃቱ በኋላ እንግዲህ የጸጥታ ኃይልም ደርሶ አስክሬን የማሰባሰብ ስራ ተሰርቷል እና ከዚያኛውም ወገን የተወሰኑ ተጎድተዋል፤ ከሸኔም ወገን ማለት በተወሰኑት ላይ እርምጃ የወሰዱ ይመስለኛል»

ጥቃቱ እንዴት ተፈጸመ ?

የአካባባው ነዋሪ መሆናቸውን የሚናገሩት የአይን ምስክር እንደሚሉት የቅዳሜ ማለዳውን በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ጉዳት  በኢትዮጵያመንግስት በሚደገፉ ሚሊሻዎች እና በኦሮሞ ታጣቂ ቡድን መካከል የተፈጠረ የተኩስ ልውውጥን ተከትሎ የመጣ ነው ይላሉ ። 

የአካባባው ነዋሪ መሆናቸውን የሚናገሩት የአይን ምስክር እንደሚሉት የቅዳሜ ማለዳውን በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ጉዳት  በኢትዮጵያመንግስት በሚደገፉ ሚሊሻዎች እና በኦሮሞ ታጣቂ ቡድን መካከል የተፈጠረ የተኩስ ልውውጥን ተከትሎ የመጣ ነው ይላሉ ። ምስል፦ Negasa Dessalegn/DW

«በዚያን ቀን ጠዋት በዚያ በኩል እያለፉ ይመስለኛል ፤ በዚያ እያለፉ ነበር ከሚሊሻ ጋር የተታኮሱ ይመስለኛል። ከዚያ በኋላ በርግጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት የማድረስ ዕቅድ የነበራቸው አይመስለኝም። በዚያ እያለፉ እያለ ሚሊሻዎቹ ተኩስ ስለከፈቱባቸው ራሳቸውን ለመከላከል ተኩስ በመክፈታቸው ነው በዚህ መሃል ሰላማዊ ሰው ላይ ጉዳት የደረሰው ። ከሁለቱም ወገን ሰዎች ተጎድተዋል። በአጠቃላይ ወደ 35 ሰዎች ይሆናሉ የተገደሉት። »
የቡለን ወረዳን ጨምሮ በመተከል ዞን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ የታጣቂዎች እንቅስቃሴአሳሳቢ መሆኑንም ነው እኚሁ የአካባቢው ነዋሪ የሚናገሩት 
 

የጸጥታው ኹኔታ አሳሳቢ ነው መባል 

« ኹኔታው አሁን በጣም ከባድ ነው። እኔ እዚያው አካባቢ ሰራተኛ ነኝ ፤ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው ከባድ ነው። ለዚህ ነገሩ ትንሽ አስቸጋሪ ነው። እንዲህ የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ  የበለጠ አስቸጋሪ እንደሚሆን ነው ።»
የህዝብ ተወካዩም ይህንኑ ሃሳብ ይጋራሉ። በአካባቢው ያለው የጸጥታ መደፍረስ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል። 
«አጠቃላይ አሁንም ስጋት ውስጥ ነው። በአጎራባች ቀበሌዎች አሁንም ስጋት ውስጥ ናቸው። ማህበረሰቡ በራሱ ሚሊሻ እየተከላከ ያለበት ሂደት ነው ያለው። የክልሉ መንግስት እና ሚዲያው አካባቢው ሰላም ነው ጸጥታ ነው ቢሉም የሸኔ እንቅስቃሴ እንደነበር ግን እናም ቀድመን እናውቅ ነበር አንድ በአንድ መሳሪያ የመንጠቅ እና ቡለን ከተማ ውስጥ ገብቶ የመውጣት ሂደት ሁሉ ነበር»


የቡለኗ ባኩጂ ቀበሌን ጨምሮ በመተከል ዞን ውስጥ ዳግም ውጥረት ያነገሰውን የጸጥታ ስጋት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ለዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሺቶ ስልክ የደወልናለቸው ቢሆንም ስብሰባ ላይ ነኝ የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።  

ለቅዳሜው ጥቃት እጁ አለበት ለተባለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው እና መንግስት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን ለቀረበበት ክስ መልስ ይሰጥ ዘንድ ለዋና አዛዡ ዋና አማካሪ አቶ ጂሬኛ ጉደታ የእጅ ስልክ ላይ አጭር መልዕክት ብናስቀምጥም መልስ ማግኘት አልቻልንም። 
በቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመተከል ዞንን ጨምሮ በክልሉ ባለፉት ጥቂት ኦመታት በተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ ሰዎች በደረሱ ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለው ሌሎች በርካቶች መቁሰላቸው ተዘግቧል። ጥቃቶቹን ተከትሎም በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ለመፈናቀል መገደዳቸው ተገልጿል። 
የክልሉ መስተዳድር በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ወደ ሰላም እንዲመለሱ ሲደረጉ የነበሩ ጥረቶች ፍሬ አፍርተው አንጻራዊ ሰላም እና መረጋጋት ማስገኘት ችለው እንደነበር ዶቼ ቬለ መዘገቡ ይታወሳል ። 

ታምራት ዲንሳ  

ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW