1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡናና ሻይ ግብይት፣ የቀይ ባሕር ቀውስ የፈጠረው ሥጋት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 9 2016

በቀይ ባሕር የንግድ መስመር ላይ የሁቲ አማፂያን በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያት ሰኔ ወር ላይ ለቀናት ቡና መላክ አቆሞ እንደነበር የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዐሳታወቀ። ይህ ሁኔታ ቡና ላኩዎች ጅቡቲ ውስጥ ላልተገባ የመጋዝን ክራይ ክፍያ እንዲጋለጡ እና ምርቱን ለከፍተኛ ወጪ በዳረገ ሌላ መስመር እንዲልኩ ማድረጉም ተነግሯል።

Äthiopien 2024 | Jahrestagung der äthiopischen Kaffee- und Teebehörde
ምስል Solomon Muchie/DW

ከቡና ግብይት የተገኘው ገቢ እና የገጠሙት ችግሮች

This browser does not support the audio element.

በቀይ ባሕር የንግድ መስመር ላይ የሁቲ አማፂያን በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያት ሰኔ ወር ላይ ለቀናት ቡና መላክ አቆሞ እንደነበር የኢትዮጵያ “የቡና መገኛ ስፍራ”ን የማልማት ጥያቄቡናና ሻይ ባለስልጣን ዐሳታወቀ። ይህ ሁኔታ ቡና ላኩዎች ጅቡቲ ውስጥ ላልተገባ የመጋዝን ክራይ ክፍያ እንዲጋለጡ እና ምርቱን ለከፍተኛ ወጪ በዳረገ ሌላ መስመር እንዲልኩ ማድረጉም ተነግሯል። ባለስልጣኑ ይህንን ችግር ለመፍታት ቡናን ለመጀመርያ ጊዜ በአውሮፕላን ከመላክ ጀምሮ በፖሊስ ታጅቦ በተሽከርካሪ እስከ ጅቡቲ መላኩን አስታውቋል።  ባለስልጣኑ ከ 30 እስከ 35 በመቶ የቡና ምርት ግብይቱን የሚከውንበት የአውሮፓ ሕብረት ሃገራት ሲሆኑ፣ ሕብረቱ ምርቱ ከደን ምንጣሮ የተገኘ ከሆነ እና በምርት ሂደቱ ሕፃናት የተሳተፉ ከሆነ እንማይቀበል በማስጠንቀቁ ይህንን ታሳቢ ያደረገ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አሳውቋል።

ከቡና ግብይት የተገኘው ገቢ እና የገጠሙት ችግሮች

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ከሆኑ ዋነኛ የግብርና ምርቶች አንዱ የሆነው ቡና በዚህ ዓመት ብቻ ወደ ስልሳ በዋናነት የአውሮፓ ሀገራት 298ሺህ 500 ቶን ተልኮ 1.43 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል ሲሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ተናግረዋል።

የተንዛዛ አሰራር በመቀነስ እና የቀጥታ ትስስር በመዘርጋት በመጠንም ሆነ በገቢ እዚህ ግባ የሚባል ያልነበረው ግብይት ላይ ማሻሻያ በማድረግ ከፍተኛ ገቢ ተገኝቷልም ብለዋል።

ባለስልጣኑ በዓመቱ ከፍተኛ የተባለውን የቡና ግብይት ገቢ ቢያገኝም፣ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የሑቲ ታጣቂ ኃይሎች በቀይ ባሕር ላይ በሚጓጓዙ እቃ ጫኝ መርከቦች ላይ በደቀኑት ከፍተኛ ሥጋት  ምክንያት ቡና መላክ ፈተና ሆኖ እንደነበርም ኃላፊው ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ወጪ በሚያስወጣው ማጓጓዣ ቡና ለመጀመርያ ጊዜ በአውሮፕላን ተጭኖ ለውጭ ግብይት መቅረቡን ገልፀዋል።

የአውሮጳ ሕብረት በቡና ግብይት ላይ ስላወጣው አዲስ ሕግ ምን ተባለ?ምስል Solomon Muchie/DW

የአውሮፓ ሕብረት በቡና ግብይት ላይ ያወጣው አዲስ ሕግ

የቡና ግብይቱ ባቡር በየጊዜው በሚገጥመው የአገልግሎት መቆራረጥ፣ በኮንቴይነር እጥረት እና በፀጥታ ችግሮችም መፈተኑ ተነግሯል። በሌላ በኩል የአውሮፓ ሕብረት ቡናን እና ሌሎች የግብርና ምርቶችን በተመለከተ አዲስ አስገዳጅ ሕግ አውጥታል። ይህም የቡና ምርት ከሚመነጠር ጫካ የሚመረት ከሆነ በሕብረቱ አባል ሀገራት ለግብይት አይውልም መባሉ አንዱ ሲሆን እድሜያቸው ለሥራ ያልደረሰ ታዳጊዎች በምርት ሂደቱ ከተሳተፉ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚቆጠር በመሆኑ በዚህ መልኩ የተገኘ ምርት አውሮፓ ውስጥ ሊሸጥ አይችልም የሚለው ሌላኛው ነው። ይህንን በተመለከተ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ዝግጅት የተጠየቁት ኃላፊው ተከታዩን መልሰዋል።

በቀይ ባሕር የንግድ መስመር ላይ የሁቲ አማፂያን በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያት ሰኔ ወር ላይ ለቀናት ቡና መላክ አቆሞ እንደነበር የኢትዮጵያ ቡናና ሻሂ ባለስልጣን ዐሳታወቀምስል Solomon Muchie/DW

"በተመነጠረ ጫካ የሚመረተው የቡና ቦቴ ስፋት ሁለት ሄክታር ነው። ይህንን ከአውሮፓ ገበያ ማውጣት የምንችልበትን ጉዳይ ከባለሃብቴች ጋር ተነጋግረንበታል" የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ እንዳሉት የቡና ግብይት ከአውሮፓ እና አሜሪካ ወደ ኤስያ አዘንብላል፣ በዚህ ዓመት ከፍተኛ መጠን ያለው የቡና ምርትም ወደ ምስራቁ የዓለም ክፍል ተልኳል።

የቡና ኮንትሮባንድ አሁንም ዋነኛ የዘርፉ ችግር  መሆኑንም ኃላፊው ገልፀዋል። ሳውዲ አረቢያ፣ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ጀርመን እና ቤልጂየም ዋነኛ የኢትዮጵያ ቡና ሸማቾች መሆናቸውም ተነግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW