1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን 20 ጉባኤና ያሳለፋቸዉ ዉሳኔዎች

ሐሙስ፣ ኅዳር 8 2015

በኢንዶኔዢያ ባሊ፤ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የተካሄደው 17 ኛው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ የጋራ መገለጫችዎችን በማውጣት ተጠናቋል። ቻድ ዛምቢያና ኢትዮጵያ ብቻ የዕዳ ክምችት ማቅለያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን አመልክተው እንደሚገኙም ተገልጿል።

Indonesien Bali Xi Jingping Georgia Meloni
ምስል Sean Kilpatrick/Zumapress/picture alliance

የዓለማችን 19 በእንዱስትሪ የበለጽጉና የአውሮጳ ህብረትን ያካተተዉ ቡድን 20

This browser does not support the audio element.

በኢንዶኔዢያ ባሊ፤ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የተካሄደው 17 ኛው የቡድን 20 የመሪዎች  ጉባኤ የጋራ መገለጫችዎችን በማውጣት ተጠናቋል። የቡድን 20 አገሮች  በዓለማችን ያሉ 19 በእንዱስትሪ የበለጽጉና ያደጉ አገሮች እንዲሁም የአውሮጳ ህብረትን ያካተተ ነዉ። ቡድኑ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር ከ 1999 ዓ.ም ጀምሮ የሚታወቅ ሲሆን በተለይ በጎርጎረሳዉያኑ 2008  ዓመት በዓለማችን ተክስቶ ከነበረው ዓለማቀፍ የፋይናንስ ቀውስ ወዲህ ግን በየዓመቱ ጉባኤዎችን በማካሄድ በዓለማቀፍ ኢኮኖሚ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በዘላቂ ልማት አጀንዳዎች ላይ የጋራ አቋሞችንና ውስኔዎችን በማሳለፍ ይታወቃል።  የቡድኑ አባላት ከደቡብ አሜሪካ፤ አርጀንቲና፤ ሜክሲኮ፣ ብራዚል፣ ከእስያና ደቡብ እስያ፤ ጃፓን፣ ቻይና፣ አውስትራሊያ፣ ደቡብ ኮሪያና  ኢንዶኔሺያ፤ ከስሜን አሜሪካ ደግሞ ዩኤስ አሜሪካና ካናዳ፣  ከአውሮጳ፤ ሩሲያ፤ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን ጣሊያንና የአውሮጳ ህብረት ሲሆኑ ከመካከለኛው ምስራቅና አፍሪቃ ደግሞ ሳኡዲ ዓረቢያና ደቡብ አፍሪቃ ናቸው።  የቡድኑ አባላት የዓለምን አጠቃይ ምርት ወይም ጂዲፕ 80 ከመቶ የሚይዙ የበጸለጸጉና ያደጉ አገሮች በመሆናቸው፤ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች ምንም እንኳ አስገዳጅነት ባይኖራቸውም በዓለም ኢኮኖሚና  የፋይናንስ ስራ ላይ የሚያሳድሩት ተጽኖ ከፍተኛ እንደሆነ ነው የሚታመነው።  
የዚህ ዓመቱ ጉባኤ የተከሂደው ግን በዩክሬን ጦርነት ምክንያት፤ አውሮጳ፤ አሜሪካንን ጨምሮ  ከሩሲያ ጋር በቀጥታም ባይሆን በግጭትና በከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጦርነት ውስጥ ባሉበት ሁኔታ፤  እንዲሁም አሜሪካና ቻይና በታይዋን ምክኒያት ተፋጠው በሚገኙበት ግዜ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገባ የኢኮኖሚ እጀንዳዎች ትኩረት ሰቶ ሊወያይና ተጨባጭ ውሳኔዎችን ለያስተላልፍ እንዳልቻለ ነው የሚነገረው።  አሜሪካና አውሮፓውያኑ ሩሲያ በዩክሬን የከፍተችው ጦረነት ለዓለም ሰላም ጭምር ስጋት የፈጠረ፤ ለተከሰተው ዓለማቀፍ የኢኮኖሚ ቀውስና የምግብ እህል እጥረትም ዋና ምክኒያት የሆነ በመሆኑ አባል አገሮቹ እንዲያወግዟትና እንዲያገሏት በግልጽ የጠየቁ ሲሆን፤ ሌሎቹ ግን ጦርነቱን ባይደግፉም ሩሲያን ከማውገዝ ግን ተቆጥበው ታይተዋል። 
የጉባኤው አስተናጋጅ የሆነችው የኢንዶኖዢያዉ ፕሬዚዳንት ጆኮ ዊዶዶ ማንንም ለይተው ሳያወግዙ ጦርነቱ ካልቆመ ግን ለሰላምና እድገት ትልቅ ችግር መሆኑን በመግለጽ የጉባኤው መሪዎች ከልዩነቶቻቸው ባሻገር በዓለማቀፍ የኢኮኖሚና የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳዎች ላይ በጋራ እንዲቆሙ ደጋግመው ሲናገሩ ተስምተዋል። ‘”ጦርነቱ ካልቆመ የዓለም እድገት ቀጣይነት አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። ጦርነቱ ካልቆመ መንግስታት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት አስቸጋሪ ነው የሚሆንባቸው።  ልንከፋፈል አይገባም፤ የቀዝቃዛው ጦርነት እንዲመጣም መፍቀድ የለብንም በማለትም አገሮች ልዩነቶቻችውን ከአጠቃላዩ ሰላምና ዕድገት አጀንዳ አንጻር በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ። 
 የጉባኤው አባላት የድሀ አገሮች የእዳ ክምችት ያሳሰባቸው መሆኑንና አበዳሪዎች የዕዳ ክምችቱ ሊቃለል በሚችልበት ሁኒታ መፍሄ እንዲያፈላልጉ ጥሪ ያቀረቡ ስለመሆኑ በጋራ መግለጫቸው ተጠቅሷል። ቀደም ሲል እንደ ጎርጎረሳዊዉ በ2020 ዓመት  የቡድን 20 እና የፓሪስ ክለብ፤ አበዳሪዎች፤ ድሀ አገሮች የኮቭድ 19 ካሳደረባቸው የኢኮኖሚ ድቀት ሊያገግሙ የሚችሉበትን ፕሮግራም ይፋ ቢያደርጉም እሳክሁን ግን ብዙም ተግባራዊ እንዳልሆነና ቻድ ዛምቢያና ኢትዮጵያ ብቻ የዕዳ ክምችት ማቅለያ ፕሮግርሙ ተጠቃሚ ለመሆን አመልክተው እንደሚገኙ ተገልጿል።  የጉባኤው አባላት በአሁኑ ወቅት  የቻድ አበዳሪዎች በቻድ የብድር የአከፋፈል ሁኔታ ላይ የደረሱበትን ስምምነትና የዛምባያንም በሚቀጥለው ዓመት ለማስተካከል መወሰናቸውን አወድሰው፤ የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ለማቃለልና የአከፋፈል ስራቱን ለማስተካከል ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ጋር የተደረሰውን ስምምነት እንደሚያበረታታቱ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። 
በሌላ በኩል ግን የቡድን 20 አገሮች በአለማቀፍ የሰላምና የኢኮኖሚ ችግሮች ዙሪያ የሚጠበቅብቸውን እያደረጉ እንዳልሆነና በየዓመቱ እየተሰበሰቡ መግለጫ ከማውጣት ያለፈ በአየር ንብረት ለውጥና የዓለም ኢኮኖሚ ኢንዲያንሰራራ በማድረግ በኩል ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ አይደለም የሚሉ ተችዎች በሰላማዊ ስልፍ ጭምር ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ተውስተውለዋል። ሌሎች ደገሞ ለምሳሌ ቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ሚስተር ዳኔል ስፔክሃርድ የቡድን 20 ስብስብና ጉባኤው፤  መሪዎች  የሁለትዮሽ ንግግሮችን በማድረግ ግንኙነቶቻችውን ለማሻሻል ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ነው የሚናገሩት። “የቡድን 20 ስብሰባዎች የጋራ መገለጫ ከማውጣት በላይ የመሪዎች የሁልትዮሽ ንግግሮች የሚካሂዱባቸውና የዓለም መሪዎች በአካል የሚገናኙባዮቸው ጥሩ መድረኮች ናቸው” በማለት ይህን መሰሉ ግንኑነት የሁልትዮሽና ዓለም አአፍ ግንኙነቶችን በረጅም ጊዘ ለማሽሻል እንደሚረዳ ያስረዳሉ። 
ቀጣዩዋ  የቡድን 20 ፕሬዚዳንትነትን የምትወስደዉ ህንድ ስትሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስተር ናሬንድራ ሞዲ ከእንዶኒዥያው ፕሬዚዳንት ሚስተር ጆኮ ዊዶዶ የፕሬዚዳንትነቱን ስልጣን ተረክበዋል።  የሚቀጥለው የቡድኑ 20 መሪዎች ስብሰባም በመጭው መስክረም ወር  በኒውዴልሂ ከተማ እንደሚሆን ከወዲሁ ተገልጿል። 
ገበያው ንጉሤ 
አዜብ ታደሰ 
ታምራት ዲንሳ
 

ምስል Kominfo KTT G20 - 2022
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW