1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህንድ የምታስተናግደው የቡድን 20 ጉባኤ

ዓርብ፣ ጳጉሜን 3 2015

የአውሮጳ ሕብረትን ጨምሮ ቡድን 20 በመባል የሚታወቁት የዓለም 20 ባለጸጋ አገሮች መሪዎች 18ኛ ጉባኤ ክነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በኒው ዴልሂ ይካሂዳል። ጉባኤው ትኩረት ሰጥቶ የሚወያየባቸው የአየር ንብረት ለውጥ፤ የዘላቂ ልማት አጀንዳዎችና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሻሻል፤ እንዲሁም የምግብ ዋስትና መረጋገጥና ሌሎችም እንደሆኑ ተገልጿል።

ፎቶ፤ የቡድን 20 ጉባኤ ኒውዴሊሂ
የቡድን 20 ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በህንድ ይካሄዳል። ፎቶ፤ የቡድን 20 ጉባኤ ኒውዴሊሂምስል Manish Swarup/AP Photo/picture alliance

ህንድ የምታስተናግደው የቡድን 20 ጉባኤ

This browser does not support the audio element.

 

የአውሮጳ ሕብረትን ጨምሮ ቡድን 20 በመባል የሚታወቁት የዓለም 20 ባለጸጋ አገሮች መሪዎች 18ኛ ጉባኤ ክነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በኒው ዴልሂ ይካሂዳል። የወቅቱ የቡድኑ ፕሬዝደንት ሕንድ ጉባኤውን ለማስተናገድ ዝግቶግቷን አጠናቃ እንግዶቹን እየተቀበለች ነው። ይህ ዘገባ እስክተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የአሜሪካኑን ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ጨምሮ በርካታ የቡድኑ አባላት አገሮች መሪዎችና ተጋብዥ እንግዶች ኒውዴልሂ መግባታቸው ተገልጿል። ሆኖም የቻይናና ሩሲያ መሪዎች በስብሰብው እንደማይገኙ ታውቋል ።የቡድን 20 ጉባኤና ያሳለፋቸዉ ዉሳኔዎች

ጉባኤው ትኩረት ሰጥቶ የሚወያየባቸው የአየር ንብረት ለውጥ፤ የዘላቂ ልማት አጀንዳዎችና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሻሻል፤ እንዲሁም የምግብ ዋስትና መረጋገጥና ሌሎችም እንደሆኑ ተገልጿል። የአፍሪቃ ሕብረት የአባልነት ጥያቄም የጉባኤው መነጋገሪያ እንደሚሆንና ውሳኔም ሳይሰጠው እንደማይቀር ተመልክቷል። ግብጽ ናይጀሪያና ሞሪሺየስ በጉባኤው እንዲገኙ ከተጋበዙ የአፍሪቃ አገሮች ውስጥ የሚጠቀሱት ናቸው።፡ የአውሮጳ ሕብረት ፕሬዝደንት ሚስተር ቻርለስ ሚሸል ዛሬ ከኒውዴልሂ በሰጡት መግለጫ ይህንኑ የአፍሪቃ ሕብረትን የአባልነት ጉዳይ «የአፍሪቃ ሕብረት የቡድኑ ቋሚ አባል መሆንን በደስታ ነው የምንቀበለው።» በማለት የሕብረቱን የአባልነት ጥያቄ ከተቀበሉት የመጀመሪያዎቹ ነበርን ሲሉ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የወቅቱ የቡድን 20 ፕሬዝደንት ሕንድ እንግዶቹን እየተቀበለች ነው። የአሜሪካኑን ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ጨምሮ በርካታ የቡድኑ አባላት አገሮች መሪዎችና ተጋብዥ እንግዶች ኒውዴልሂ ገብተዋል። ፎቶ፤ የአሜሪካን ፕሬዝደንት ጆ ባይደንምስል Evan Vucci/AP/dpa/picture alliance

ይሁን እንጂ ጉባኤውን የዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ይጫነዋል እየተባለ ነው። የጉባኤው አስተናጋጅ ህንድ በዩኪሬን ጦርነት ምክንያት አውሮጳና አሜሪካ ካወገዟትና ማዕቀብም ከጣሉባት ሩሲያ ጋር ከፍተኛ የንግድ ግንኙነት ያላት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ ጉባኤው ከፖለቲካና የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ይልቅ በዓለም አቀፍ ግንኑነቶችና የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ላይ እንዲያተኩር ትፈልጋለች ነው የሚባለው። ጠቅላይ ሚንስተር ኒያንድራ ሞዲ በአውሮጳና አሜሪክ በሚደረጉ ጉባኤዎች የማይጠፉትን የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪን በዚህ ጉባኤ አለመጋበዛቸው፤ ዘንለንስኪን ብቻ ሳይሆን የምዕራብ መንግሥታትንም ሳያስከፋ እንዳልቀረ ይገመታል። ሆኖም ግን ፕሬዝደንት ሞዲ ይህን ያደረጉት ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኑነት እንዳይሻክር ብቻ ሳይሆን፤ የህንድን ገለልተኛ አቋም ለማስረገጥም እንደሆነ ነው የሚነገረው። ቢሆንም ግን የዩክሬን ጉዳይ ዋና የስብሰባው ትኩረት እንዲሆንና የጉባኤው መግለጫዎችም ሩሲያን የሚያወግዙ እንዲሆኑመሐደረ ዜና፣ ሁለቱ ጉባኤዎች የምዕራባውያኑ ፍላጎት ነው። ከአንድ ቀን በፊት ስለ ጉባኤው ሂደትና ተጠባቂ ውጤቶች እዚህ ብራስልስ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ አንድ ስማቸው እንዳይይጠቀስ የፈለጉ ከፍተኛ የሕብረቱ ባለሥልጣን እንዳስታወቁት፤ ህንድ ያቅረበችው የጋራ መግለጫ ረቂቅ፤ የሩሲያን ወራሪነት በግልጽ ቋንቋ ያላስቀመጠና የሕብረቱን አቋምና ፍላጎት የማያንጸባርቅ በመሆኑ እንዲሻሻል ጠይቀው ድርድር እየተደረገ እንደሆነ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ ጉባኤውን የሚከታተሉት ተንታኞች እንደሚሉት በዚህ አጀንዳ ላይ የዘንድሮው የቡድን 20 ጉባኤ ሁሉም የጉባኤው አባል አገሮች የሚስማሙበት የጋራ መግለጫ መውጣቱ አጠራጣሪ ነው።

የቡድን 20 አገሮች የዓለማችን አጠቃላይ ምርት (ጂዲፒ) 80 ከመቶ የሚመረትባቸው፤ የዓለማችን ንግድ 75 ከመቶ የሚሳለጥባቸው፤ እንዲሁም ከዓለማችን ህዝብም ሁለት ሦስተኛው የሚኖርባቸው ናቸው። ፎቶ፤ የቡድን 20 ጉባኤ ዝግጅት ኒውዴሊህምስል Hindustan Times/IMAGO

በጉባኤው የሩሲያ በተለይም የቻይና መሪ አለመገኘት እንግዳ ነገር ሆኗል። የቻይና ፕሬዝደንት በጠቅላይ ሚኒስትራቸው ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው የሚወከሉ ቢሆንም፤ የሁለቱ በተለይም የቻይናው መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡድን 20 ጉባኤ አለመገኘት የሚኖረው አንድምታ እያነጋገረ ነው። በአትላንቲክ ካውንስል የጂኦ ኢኮኖሚክስ ማዕከል ዳይሬተር የሆኑት ጆሽ ሊፕስኪም በቡድን 20 ታሪክ የቻይና መሪ ያልተገኘብት ይህ የኒውዴልሂው እንደሆነ ነው የገለጹት።  በሌላ በኩል የቻይናው መሪ አለመኖር በተለይ ለፕሬዝደንት ባይደን በጉባኤው ተጽኖ ለመፍጠርና በደቡባዊው የዓለማችን ክፍል ካሉት አገሮች ጋር ያለውን ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ጥሩ አጋጣሚ ሊሆንላቸው ይችላልም እየተባለ ነው። ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ለጎን የተለያዩ የሁለትዮሽና የቡድን ውይይቶች እንደሚካሂዱ ይጠበቃል። አጋጣሚውም የጉባኤው አስተናጋጅ ሀገር ህንድ ግንኙነቷን ለማስፋት፤ በዓለም አቀፉ ፖለቲካ ተሰሚነቷንና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷንም ለማሳየት ጥሩ መድረክ እንደሚሆንላት እየተገለጸ ነው። የቡድን 20 አገሮች የዓለማችን አጠቃላይ ምርት (ጂዲፒ) 80 ከመቶ የሚመረትባቸው፤ የዓለማችን ንግድ 75 ከመቶ የሚሳለጥባቸው፤ እንዲሁም ከዓለማችን ህዝብም ሁለት ሦስተኛው የሚኖርባቸው ናቸው።ትኩረቱን በዩክሬኑ ጦርነት ላይ ያደረገዉ የቡድን 20 ጉባኤ
ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW