ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች
ዓርብ፣ ኅዳር 3 2014ማስታወቂያ
ወጣት ኦልብራይት ወ/መስቀል እና መድሃኒት ብረሃኑ በሀዋሳ ከተማ ወሊማ በተባለው የሲዳማ የባህል ቡድን አባል በመሆን ባህላዊ ውዝዋዜ እያቀረቡ ከሚገኙ የቡድኑ አባላት መካከል ናቸው። ወጣቶቹ በቡድኑ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ የጀመሩት ለባህላዊ ጭፈራ ባደረባቸው ፍቅር የተነሳ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ዘርፉ የገቢ ምንጭ ጭምር እየሆናቸው እንደሚገኝ ይናገራሉ ። አንድ ቀን ሀገራቸውን ወክለው ባህላቸውን ማስተዋወቅ ይሻሉ።የሀዋሳ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢያችን ሊሻን ዳኜ ከወጣቶቹ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጋለች።
ሊሻን ዳኜ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ