1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባሕርዳር ሕዝብ ጥያቄና ተቃዉሞ

ማክሰኞ፣ ጥር 19 2012

የተለያዩ መፈክሮችን አንግቦ ባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም የተሰበሰበዉ ሰልፈኛ የፌደራሉ እና የዓማራ ክልል መንግስታት ባለስልጣናትን ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ አልጣሩም በማለት ነቅፏቸዋልም።

Bahir Dar Demonstration Amhara Region Äthiopien
ምስል DW/A. Mekonnen

ተማሪዎች እንዲለቀቁ የባሕርዳር ሕዝብ በሰልፍ ጠየቀ

This browser does not support the audio element.

 ከደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ወደየቤተሰቦቻቸዉ ሲጓዙ እስካሁን ማንነታቸዉ ባልታወቀ  ሰዎች የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ የባሕርዳርና የአካባቢዉ ሕዝብ ባደባባይ ሰልፍ ጠየቀ። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ተማሪዎቹ ተለቅቀዋል በማለት የሐሰት መረጃ ማሰራጨታቸዉን ሰልፈኛዉ አዉግዟል።የተለያዩ መፈክሮችን አንግቦ ባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም የተሰበሰበዉ ሰልፈኛ የፌደራሉ እና የዓማራ ክልል መንግስታት ባለስልጣናትን ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ አልጣሩም በማለት ነቅፏቸዋልም።ዉግዘትና ነቀፋ የተፈራረቀባቸዉ የፌደራሉና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ስለ ጉዳዩ እስካሁን በይፋ ያሉት ነገር የለም።ባለፈዉ ሕዳር ማብቂያ የተጋቱት ተማሪዎች እንዲለቀቁ ዘመቻ የጀመሩት ወገኖች እንደሚሉት አጠቃላይ ታጋቾቹ  17 ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ሴቶች ናቸዉ።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW