1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤተእስራኤላውያን አዲስ መንደር ምስረታ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 29 2015

"ቡዳ ይሉናል፤ ጅብ ይሉናል፤ሌሊት ሌሊት ወደ ጅብነት የሚቀየሩ ይሉናል። 3,000 ዓመታት በኖርንበት አገር ውስጥ ፈላሻ የሚለው ስም መሬት አልባ ለማለት ነው። እዚህ አገር ላይ መሬት የላችሁም ፈልሳችሁ ነው የመጣችሁት የሚል ነው። ይህ ስም ማጠልሸት የስንቱን ትዳር ያናጋና ብዙ ማሕበራዊ ቀውስ ያመጣ ነው።"

Äthiopien | Jüdische Gemeinschaft
ምስል M. Asefa

የቤተ-እስራኤላውያን መንደር ምስረታ

This browser does not support the audio element.

በሰሜን ሽዋ በተለያዩ ወረዳዎች ተበትነው እምሮአዊና አካላዊ የጤና ችግር ላለባቸዉ  ቤተእስራኤላውያን ጤናማ የሰፈራ መንደር ለመመስረት የተጀመረው ፕሮጀክት። ቤተ-እስራኤላውያን ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በ3 ዙሮች እንደሆኑ በጉዳዩ ላይ ሁለት መጽሐፎችን ያሳተሙት የቤተእስራኤላውያን የኦሪት እምነት ማሕበረሰብ ስራ አስኪያጅና እና የሰሜን ሽዋ የቤተእስራኤላውያን የሰፈራ መንደር ፕሮጀክት ፕረዚደንት መምህር በላይነህ ታዘብኩ ይገልጻሉ። ጎንደር ደምቢያ ማዕከል አድርገውም ወደ ተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እንደ ተንቀሳቀሱም አክለዋል። ቤተ እስራኤላውያኑ በአገሪቱ ታሪክ የራሳቸውን አሻራ እንዳኖሩም  ያስረዳሉ።
«ወርቅ ላበደረ ጠጠር ሆነና ነገሩ» ይላሉ መምህር በላይነህ በአገሪቱ ግንባታ የራሳቸውን ሚና ለተጫወቱት እና በመጫወት ላይ የሚገኙት ሕዝቦች የተሰጣቸው ስምና መገለል ግን ሥነ አእምሮዊ እና አካላዊ የጤና ችግር እንዳስከተለባቸው የገለጹት መምህ በላይነህ ማብራሪያቸውን ሲቀጥሉ።
"ቡዳ ይሉናል፤ ጅብ ይሉናል፤ሌሊት ሌሊት ወደ ጅብነት የሚቀየሩ ይሉናል። ካይላt፣ ቂሌ የተለያዩ ስሞች አሉ የተሰጡን። 3,000 ዓመታት በኖርንበት አገር ውስጥ ፈላሻ የሚለው ስም መሬት አልባ ለማለት ነው። እዚህ አገር ላይ መሬት የላችሁም ፈልሳችሁ ነው የመጣችሁት የሚል ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ የምትኮራባቸው ሦስቱ ሐይማኖቶች ኦሪት፣ ከዛክርስኅና ከዛ ክርስትና እነዚህ ሐይማኖቶች ከውጭ እንደመጡ ይታወቃል። የኛን ብቻ ነው ፈልሶ እንደመጣ ተደርጎ የሚወሰደው። የተመቸ የንሮ ታ፣ ማምለኪያ ቦታዎች፣ የቀብር ቦታዎች እንዳይኖረው ማድረግ፤ ይህ ስም ማቸልሸት የስንቱን ትዳር ያናጋና ብዙ ማሕበራዊ ቀውስ ያመጣ ነው።"
የሚገርመው የአፍሪቃ መዲና በምትባለው አዲስ አበባ የሚኖሩ ቤተእስራኤላውያን እስከዛሬዋ ድረስ ሞተው የሚቀበሩበት ቦታ እንኳን የላቸውም። ሞተው እንደሰው የመቀበር ዕድልን ለማግኘት ከሚኖሩበት አካባቢ ሐይማኖት ጋር ተመሳስለው እና ማንነታቸውን አጥፍተው ጭምር እንደሆነ መምህር በላይነህ በምሬት አጫውተውናል። 
ቡተእስራኤላውያን በማሕበረሰቡ በሚደርስባቸው አድልኦ እና መገለል ምክንያት፤ ተከትሎ የመጣውን የሥነ አዕምሮአዊና አካላዊ ችግሮች በመቅረፍ ፈር ቀዳጅ ይሆናል የተባለለት ፕሮጀክት በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን ደብረብርሐን አካባቢ  እውን ሊሆን ጫፍ የደረሰ ይመስላል። የሰሜን ሽዋ ቤተእስራኤላውያን የመንደር ምስረታ። የፕሮጀክቱ ሰብሳቢ ዶክተር አክሊሉ ተፈራ።
"የፕሮጀቱ ዓላማ ቤተ እስራኤላውያን በመንደር ተሰባስበው ጤናቸው ተጠብቆ፤ ጽዱና ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት እና ትምህርት ቤት በመገንባት የተሻለ ኑሩ እንዲኖሩ ማስል ነው። "
የቤተእስራኤላውያን አንዱና ትልቁ ችግር ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት አለማግኘት ነው። በዚሁ ምክንያት ሕይወቷን ያጣች ወላጅ እናት፤ ሕጻን አዛውንቱ ቤት ይቁጠረው ብሎ ማለፍ ሳይሻል አይቀርም። ይህን ችግር ለመቅረፍ ግዙፍ ሆስፒታል መገንባት የፕሮጀክቱ አካል እንደሆነ ዶክተር አክሊሉ ነግረውናል።
ቤተእስራኤላውያን አዲስ አበባን ጨምሮ በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የመጸዳጃና የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚያገኙት ዝቅተኛ ሊባል በሚችል ደረጃ መሆኑን የገለጹት መምህር በላይነህ በደብረብርሃን የሚሰሩ መኖሪያ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁና የነበሩባቸውን ችግሮች የሚፈቱ እንደሚሁኑ ገልጸውልናል።
ትኩረት ተነፍጎአቸው በአስከፊ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ቤተእስራኤላውያን ተገቢው ትኩረትና ክብር ሊሰጣቸዉ እንደሚገባ ባለጉዳዮች ያሳስባሉ።
በሰሜን ሽዋ በቅርቡ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የቤተእስራኤላውያን መንደር ምስረታና ዘመናዊ ሆስፒታል ግንባታ አስመልክተን ያዘጋጀነዉን ጥንቅር የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!


ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW