1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዘረኝነት ጥቃት ቤተ-እስራኤላዉያን ላይ

ሐሙስ፣ ጥር 23 2011

ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ ወጣት ዳንኤል ሰለሞን ለDW በስልክ እንደነገረን የእስራኤል ፖሊስና ባለሥልጣናት ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያንን ሲግድሉና ሲበድሉ የሰሞኑ የመጀመሪያዉ አይደለም።                           

Israel Proteste gegen Polizeigewalt in Tel Aviv
ምስል Reuters/A. Awad

(Q&A) Danel-Ethiopian Israelis - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

የእስራኤል ባለስልጣናትና ፖሊስ በኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉን ላይ ይፈፅሙታል የሚባለዉን የዘር ጭቆናና ግድያን በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን እስራኤላዉያን ትናንት ባደባባይ ሠልፍ ተቃዉሙ።ቴሌአቪ ዉስጥ አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ ከሁለት ሳምንት በፊት የሁዳ ቢያድጋ የተባለዉን ኢትዮጵያዊ እስራኤላዉ የአዕምሮ በሽተኛ ወጣት በጥይት ደብድቦ የገደለዉ ፖሊስ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቋልም።ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ ወጣት ዳንኤል ሰለሞን ለDW በስልክ እንደነገረን የእስራኤል ፖሊስና ባለሥልጣናት ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያንን ሲግድሉና ሲበድሉ የሰሞኑ የመጀመሪያዉ አይደለም።በእስራኤል ምክር ቤት የሰብአዊ ሐብት ሎጂስቲክ አስተባባሪ አቶ ዮናታን ታከለ እንደሚሉት በኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያን ላይ የሚፈፀመዉ ግድያና በደል እንዲቆም ሕዝቡ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም እስካሁን ሁነኛ መፍትሔ አላገኘም።አቶ ዮናታን እንደሚሉት  በቅርቡ የ24ት ዓመቱን  የዐዕምሮ ሕመምተኛ ወጣት የገደለዉ ፖሊስ ለፍርድ አለመቅረቡ ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያንን በጅጉ አስቆጥቷል።አቶ ዮናታንን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።ሟቹ ከዚሕ ቀደም የእስራኤል ጦር ሠራዊት ባልደረባ ነበር።የትናንትናዉን ሠልፍ ያስተባበሩት እንደገለጡት ሟቹ ከቤቱ ስለት ይዞ ሲወጣ  ፖሊስ እንዲረዳቸዉ ሥልክ ደዉለዉ የጠሩት ቤተሰቦቹ ናቸዉ።ለርዳታ የተጠራዉ ፖሊስ የዐዕምሮ ሕመምተኛዉን ወጣት በጥይት ደብድቦ ገደለዉ።

ምስል Reuters/A. Awad

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW