የቤት ሰራተኞችንና አሰሪዎችን የሚያገናኘው ድረ ገፅ
ሐሙስ፣ መጋቢት 21 2015
ሞግዚት ወይም የቤት ሰራተኛ በቀላሉ የሚገኙበት ድረገፅ በርካታ ችግሮችን እየቀነሰ ነው ተብሏል። የሞግዚትም ሆነ የቤት ሠራተኛ ችግር ባየለባቸው ከተሞች ችግሩን ለመቀነስ አንዲት ወጣት የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የደረሰችበትን ይህንኑ መፍትሄ ቀጣዩ የሀና ደምሴ ዘገባ ይመለከታል። ኢትዮጵያ በተለይ በከትሞች አካባቢ ሴቶች ወልደው የወሊድ ፍቃዳቸውን ከጨረሱ በኋላ ልጆችን ተንከባክቦ የሚጠብቅ አጋዥ በጣም ይችገራሉ ። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደሞ በልጅ አሳዳጊነት ወይም በቤት ሰራተኝነት ገብተው ልጆችን እየሰረቁ የሚሰዉሩ እና ገንዘብ አምጡ የሚሉ ቁጥራቸው የጨመረ በመሆኑ የሁሉም እናቶች ማለት በሚያስችል ሁኔታ ልጄን ለማንጥዬ ወደስራ እመለሳለሁ የሚል ስጋት አይሏል። ።ይህንን ክፍተት የተመለከተች አንዲት ወጣት ቴክኖሎጂን በመጠቀም አንድ የመፍትሄ መንገድ አምጥታልች፤ ሞግዚት ዶት ኮም የተባለ ሞግዚት ወይም የቤት ሰራተኞችን ከአሰሪዎች ጋር የሚያገናኝ ድረገጽ ። ስራ ፈላጊዎችን በመሰብሰብ እና አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት ድረገፁ ላይ ትመዘግባለች አገልግሎቱን ፈላጊ ድረገፁ ላይ በመሂድ በሚፈልጉት መስፈርት መሰረት ባለሙያዎችን ያገኛሉ።
ይህ ድረገፅ የሰራተኞችን ሙሉ መረጃ የያዘ ከቅድሞ ቀጣሪያቸው የተሰጣቸውን ግብረ መልስ እና ዋስትናም ያካተተ በመሆኑ ቀጣሪዎች ያለ ምንም ችግር እና የደህንንነት ስጋት ባለሞያ ማግኘት ይችላሉ። ይህንን ዘመናዊ የሰራተኛ እና አስሪ መገናኛን የሰራችው ውጣት ሳምራዊት ነች ።
«በተለያዩ አጋጣሚዎች አግኝቼ የማነጋግራቸው ድርጅቶች እና አሰሪዎች ስራውን አክብሮ የሚሰራ ባለሙያ ተቸገርን ይላሉ በሌላ በኩል ደግሞ ተምሬ ተመርቄ ስራ ማግኘት አልቻልኩም የሚሉ እና በስራ ማጣት የተቸገሩ ብዙ ወጣቶችን ይገኛሉ ፤ያኔ ነው እኔ ይ ለዚህ ችግር ድልድይ በመሆን ልዩነቱን የሚቀንስ አገልግሎት መስጠት አለብኝ በሚል የጀመርኩት። አሁን ቴክኖሎጂ የብዙዎችን ህይወት አቅልሏል። ስለዚህ ነውእኔ ባለሞያዎችን በማብቃት እና የቴክኖሎጂ ብልሀቱን በመስራት ለፈላጊዎች ማቀረብ የጀመርኩት»ብላለች
ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር