1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ይቅርታ

ሐሙስ፣ የካቲት 4 2013

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ  በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግሮች ምክንያት በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰው ሞት እና ከቤት ንብረት መፈናቀል አስመልክቶ  ይቅርታ ጠይቋል።

Karte Äthiopien Metekel EN

«ከይቅርታው ጎን ኅብረተሰቡ ሊካስ ይገባል»

This browser does not support the audio element.

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ  በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግሮች ምክንያት በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰው ሞት እና ከቤት ንብረት መፈናቀል አስመልክቶ  ይቅርታ ጠይቋል። ፓርቲው ይቅርታ የጠየቀው ለአራት ቀናት ካከሄደው ጉባኤ በኋላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ሲሆን የመተከል ዞን የተፈጠረው ችግርም የሕዝብ ሳይሆን የአመራሩ መሆኑን የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱል ቃድር ከትናንት በስቲያ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል። የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታደለ ተረፈን ከብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማገዱንም ፓርቲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመልክቷል። በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችም መንግሥት ለወደመባቸው ንብረት ካሣ እንዲቀፍላቸውና ወደ ቀአቸውም እንዲመልሳቸውም ጠቁመዋል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW