1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤንዚን እጥረትና መንስኤው 

ሰኞ፣ ሚያዝያ 4 2013

ያነጋገርናቸው የነዳጅ ጫኝ ቦቴ አሽከርካሪ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች ተከስቶ የነበረው ግጭት በነዳጅ ማጓጓዝ ሥራ ላይ እክል ፈጥሮ የ3 ቀናት መዘግየት ማስከተሉን ለዶቼቬለ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እንደሚለው ደግሞ መጋቢት 29 ቀን በሁለቱ ክልሎች በተፈጠረው ችግር መስተጓጎል ተፈጥሮ እንጂ መሰረታዊ የነዳጅ አቅርቦት ችግር የለም ።

Äthiopien Addis Abeba Benzinrationierung
ምስል Solomon Muchie/DW

የቤንዚን እጥረትና መንስኤው 

This browser does not support the audio element.

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የነዳጅ በተለይም የቤንዚን እጥረት ተከስቷል።ቤንዚን ለማግኘት ተሽከርካሪዎች ረጃጅም ሰልፍ ለመጠበቅ ተገደዋል። 
ያነጋገርናቸው የነዳጅ ጫኝ ቦቴ አሽከርካሪ  በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ተከስቶ የነበረው ግጭት በነዳጅ ማጓጓዝ ሥራ ላይ እክል ፈጥሮ የሦስት ቀናት መዘግየት ማስከተሉን ለዶቼቬለ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እንደሚለው ደግሞ መጋቢት 29 ቀን በሁለቱ ክልሎች በተፈጠረው ችግር መስተጓጎል ተፈጥሮ እንጂ መሰረታዊ የነዳጅ አቅርቦት ችግር የለም ።ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ በፈጠረው ሥጋት ሱዳን ድንበሯን በምድርም በዓየርም ከዘጋች ጀምሮ የነዳጅ ፍጆታዋን ሙሉ በሙሉ በጅቡቲ በኩል እንደምታስገባ የተናገረው ይሄው ድርጅት ከጅቡቲ የሚገባው ነዳጅ በድሬዳዋ እና በአፋር በኩል ወደ መሃል ሀገር ይገባል ብሏል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW