1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤንዚን እጥረት የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን አማረረ

ሐሙስ፣ መጋቢት 22 2014

ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪዎች ነዳጅ በፈረቃ አንዲያገኙ ለማድረግ የተገደድሁት አሁን ባጋጠመው የቤንዚን አጥረት የተነሳ ነው ይላል።  አሽከርካሪዎች፦ አስተዳደሩ በቀን ቤንዚን አልቋል እያሉ በምሽት በበርሜል በሚቸበችቡ ማደያዎች ላይ ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል። 

Äthiopien Benziknappheit in Hawassa
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ቤንዚን አልቋል እያሉ በምሽት በበርሜል የሚቸበችቡ አሉ

This browser does not support the audio element.

«ጠዋት ሞኖፖል የሚባል ማደያ አለ፤ እዚያ ተሰለፍኩ። እዚያ ጋር ረብሻ ተከስቶ መጣሁ» የቤንዚን እጥረት ያማረራቸው የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ ምሬት ነው። «ኖክ ተሰለፍኩ፤ እዚያም ተዘጋ» ያሉት እኚህ ነዋሪ ነዳጅ ከቀዱ ሥራ ካቆሙም ሳምንት እንደሆናቸው በምሬት ይናገራሉ።  በርካቶች ተመሳሳይ ምሬት ሲያሰሙ ይደመጣል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ አሽከርካሪዎች ምርቱን በፈረቃ አንዲያገኙ ለማድረግ የተገደድሁት አሁን ባጋጠመው የቤንዚን አጥረት የተነሳ ነው ይላል።  አሽከርካሪዎች፦ አስተዳደሩ በቀን ቤንዚን አልቋል እያሉ በምሽት በበርሜል በሚቸበችቡ ማደያዎች ላይ ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል። 

በሐዋሳ ከተማ ከቅርብ ጊዜያት አንስቶ ቤንዚን ለመቅዳት ረዣዥም ሰልፎችን መመልከት የተለመደ ጆኗል። የቤንዚን እጥረት በተለይ በቀን ገቢያቸው ለሚተዳደሩ ባለሦስት እግር የባጃጅ አሽከርካሪዎች ኹኔታው አስቸጋሪ እንደሆነ ይናገራሉ። 

በአዲሱ አሠራር መሠረት የተሽከርካሪዎቹ ሠሌዳ የመጨረሻ ቁጥራቸው ሙሉ እና ጎደሎ በሚል በፈረቃ እንዲስተናገዱ እያደረገ እንደሚገኝ የከተማው የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገልጿል። አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬል (DW)የሰጡ የከተማይቱ አሽከርካሪዎችና ሞተረኞች በበኩላቸው ቤንዚን ለመቅዳት ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በማደያዎች እንደሚሰልፉ በመጥቀስ መመሪያው የዘረጋው አሠራር በሠልፉ የሚደርሰውን እንግልትና ጊዜን ለመቆጠብ ይረዳል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ መምሪያው በቀን ቤንዚን አልቋል በማለት በጭለማ በበርሜል በሚቸበችቡ የማደያ ድርጅቶች ላይ ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል። የአሽከርካሪዎቹና የሞተረኞች አስተያየት እውነትንት ያለው ነው ያሉት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ በላይነሽ ገዳ አስተዳደሩ በከተማው የተለያዩ አካባቢዎች ቤንዚን በበርሜል አከማችተው ሲሸጡ የተገኙ ግለሰቦችን በቁጥጥር እያዋለ፣ ቤንዚናቸውንም እየወረሰ ይገኛል ብለዋል።

ጭለማን ተገን በማድረግ ለሕገ ወጥ ቸርቻሪዎች በበርሜል ሽያጭ ይካሄዳል የተባለውን ለመቆጣጠር የማደያ ድርጅቶች ሽያጭ ከመጀመራችው በፊትና በኋላ በተቋቋመው 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW