1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔራዊ ፈተና ዝግጅት

ረቡዕ፣ ግንቦት 14 2011

ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱትን የአስረኛ እና የ12ኛ ክፍሎች ተማሪዎችን በስርዓት ለማስፈተን ከፀጥታ ቁጥጥር እስከ መፈተኛ ሥፍራዎች ያሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን የትምሕርት ሚንስቴር ባለስልጣናት አስታዉቀዋል።

Äthiopien National Examination Agency in Addis Abeba | Araya Gebregziabher, Direktor
ምስል DW/S. Muchie

የብሔራዊ ፈተና ዝግጅት

This browser does not support the audio element.


ሰኔ ባተ-ፈተና መጣ ነዉ ለተማሪ።ሰኔ ሁለት ሳምንት ይቀረዋል።ዝግጅቱ ግን፣ የተፈታኞቹን ባናቅዉም ፈታኞቹ አጠናቅናል ብለዋል።በተለይ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱትን የአስረኛ እና የ12ኛ ክፍሎች ተማሪዎችን በስርዓት ለማስፈተን ከፀጥታ ቁጥጥር እስከ መፈተኛ ሥፍራዎች ያሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን የትምሕርት ሚንስቴር ባለስልጣናት አስታዉቀዋል።የዘንድሮዉ ፈተና ከእስከ ዛሬዉ በሶስት ምክንያቶች ይለያል።አንደኛ ወቅቱ-ከግንቦት ወደ ሰኔ መሸጋሸጉ፣ ሁለተኛዉ በርካታ ተማሪዎች መፈናቀላቸዉና ሶስተኛዉ የፀጥታ ሥጋት ናቸዉ።የፈተናዉ አዘጋጆች እንደሚሉት ለሁሉም መፍትሔ አብጅተዋለታል።ዘንድሮ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የ10ኛ ክፍል እና ከ3 መቶ ሃያ ሺሕ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ይፈተናሉ።

 

 ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW