1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ትምህርትሰሜን አሜሪካ

የ"ብሩህ ትውልድ" የልዩ ክህሎት ሥልጠና በኢትዮጵያ

ታሪኩ ኃይሉ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 28 2017

በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በ28 ማዕከላት ከ800 በላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የክረምት ልዩ የክህሎት ስልጠና ለመስጠት መዘጋጀቱን ብሩህ ትውልድ ድርጅት አስታወቀ። የብሩህ ትውልድ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች ለሃገራቸው መሰረታዊ ችግሮች መፍትሄ የሚያፈላልጉና ዐዲስ ነገር መፍጠር የሚችሉ ዜጎችን ማፍራት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በ28 ማዕከላት ከ800 በላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የክረምት ልዩ የክህሎት ስልጠና ለመስጠት መዘጋጀቱን ብሩህ ትውልድ ድርጅት አስታወቀ።ምስል፦ Wolaita Sodo University

የ"ብሩህ ትውልድ" የልዩ ክህሎት ሥልጠና በኢትዮጵያ

This browser does not support the audio element.

"ብሩህ ትውልድ"፣በዲያስፖራ ባለሙያዎችና ዓለም አቀፍ በጎ ፈቃደኞች የሚንቀሳቀስና በቨርጂኒያ ግዛት የተመዘገበ ድርጅት ነው። ከሦስት ዓመት በፊት፣እንደ ጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር 2022 ክረምት ወቅት፣በኢትዮጵያ ዘጠኝ አካባቢዎች በ110 ተማሪዎች የተጀመረው የድርጅቱ ስልጠና፣ከአንድ ዓመት በኃላ ተደራሽነቱን ከአራት እጥፍ በላይ ለማስፋት ችሏል።

ዘንድሮ በአራተኛ ዓመቱ፣ ከ800 በላይ  በትምህርት ውጤታቸው ብልጫ ያመጡ ተማሪዎች በ28 ማዕከላት ለፕሮግራሙ ተመርጠዋል።

 ዐለም አቀፍ በጎ ፈቃደኞች በበይነ መረብ አማካይነት የሚሰጡት ይህ ስልጠና በእንግሊዝኛ ተግባቦት፣ በንባብ፣ በሂሳዊ አስተሳሰብ፣ በአመራር፣በችግር አፈታትና በልዩ ልዩ የማኀበረሰብ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን የድርጅቶ በጎ ፈቃደኛ አስተባባሪዎች ገልጸውልናል።

«በትግራይ ከመቶ 50 ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል» የትግራይ አስተዳደር

በኮሎራዶ ነዋሪ የሆኑት አቶ ወልደ ዮሐንስ አሰፋ፣ የ"ብሩዕ ትውልድ"፣ በጎ ፈቃደኛ መምህርና ፕሮግራም አስተባባሪ ናቸው።

የትምህርት አሰጣጥ

"በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ላሉ የ10ኛና የ11 ክፍል ተማሪዎች ማስተማር ነው፤ በበይነ መረብ ነው የሚካሄደው።ካለንበት ቦታ ከአሜሪካም ይሁን ከአውስትራሊያም ይሁን  ከእንግሊዝ አገርም ይሁን፣ ከተለያዩ አገሮች ለዚህ አርአያ ለተገዙ ሰዎች መድረክ ሰጥቶ ማስተማር ነው።"

የብሩህ ትውልድ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች ለተማሪዎች የሚሰጡት ሥልጠና በበይነ መረብ አማካኝነት የሚቀርብ ነውምስል፦ picture-alliance/AP Photo/E. Risberg

በኢትዮጵያ የብሩህ ትውልድ ኘሮግራም ዋና አስተባባሪ ፋሲካ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ክልሎች የስልጠና መርሐ ግብሩ ተሳታፊ መሆናቸውን ገልፀዋል።

" ሁሉም ክልሎች ላይ የምንሰራ ሲሆን፣በእኛ መስፈርት መሰረት አንድ ተማሪ መስፈርታችንን ያሟላ ከሆነ ቃለምልልስ ተደርጎ ወደዚህ ፕሮግራም ይቀላቀላል ማለት ነው።"

ተማሪዎቹ በዚህ መርሐ ግብር የሚሳተፉት፣ መደበኛ የትምህርታቸውን ጊዜ ካጠናቀቁ በኋላ በሚኖራቸው የክረምቱ ወቅት ላይ መሆኑንም አስረድተዋል።

" ተጨማሪ ነው፤ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በክረምት ያላቸውን ጊዜ እንዲጠቀሙ ነው የምናደርገው። ስለዚህ ያላቸውን ጊዜ ይጠቀማሉ፣ ማኀበረሰባቸውን እየጠቀሙ ራሳቸውን የሚቀይሩበት ፕሮግራም ነው።"

በመርሐ ግብሩ የተገኙ ውጤቶች

"ብሩህ ትውልድ"፣የአራተኛው ዓመት መርሐግብርን በቅርቡ ያስጀመረ ሲሆን፣ይህ የስልጠና መርሀግብር ከዚህ ቀደም በተማሪዎች እና በማኀበረሰቡ ሕይወት ላይ ለውጥ እያመጣ መሆኑን፣ አቶ ወልደ ዮሐንስ ይናገራሉ።

የጀርመን ቤተ ክርስቲያን ት/ቤት ለተማሪዎቹ ምገባ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱ

"እንደው በራሴ እንኳን በአርባ ምንጭ ያለው፣እንደ ማይክሮ ፋይናንስ ለምሳሌ የተሰራ ነው።ሌላ ደግሞ ብዙ ዐይነት ችግርን የቀረፈና ለማኀረሰቡ በተለያየ መንገድ አስተዋጽኦ ያደረገ ነው።"

በኢትዮጵያ የፕሮግራሙ አስተባባሪም፣ ተማሪዎቹ ላይ ስለታየው ለውጥ ተጨማሪ አስተያየት አላቸው።

 "ችግርን የመቅረፍ የማየት በአካባቢያቸው ላይ ያላቸው አቅም አለ።ፕሮግራሙን ሲጨርሱ ከመጻፍና ማንበብ ክሎታቸው በተጨማሪ፣ በደንብ አዳብረው መጨረሻ ላይ የሚታይ ውጤት የሚያሳዩ ናቸው።"

የተማሪዋ አስተያየት ስለፕሮግራሙ ጠቀሜታ

በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣የልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ሲያም ሚፍታ ፣በዚህ መርሐ ግብር በመሳተፏ ምን ጠቀሜታ እንዳገኘች ጠይቀናት፣ እንደሚከተለው መልሳለች።

"ጠቀሜታዎቹ በጣም ብዙ ናቸው። ክፍል ውስጥ በምንማርበት ጊዜ የቤት ስራና የሚቀርቡ ሥራዎች ይሰጡናል።  በራስ መተማመን በደንብ እንዳዳብርና ሰዎች ፊት ለፊት ያለ ፍርሃት እንዳወራ ጠቅሞኛል። በተጨማሪ ደግሞ ንግግር አቅርቤ ነበር፤ ይህ ደግሞ የበለጠ በብዙ ሰዎች ፊት ለፊት ቆሜ ለማውራት ችሎታዬን ጨምሮኛል::"

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW