1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የንጉስ ሳልሳዊ ቻርልስ የጀርመን ጉብኝት

ሐሙስ፣ መጋቢት 21 2015

ንጉስ ሳልሳዊ ቻርስ ዛሬ በጀርመን ፓርላማ ባሰሙት ንግግር ሁለቱ ሀገራት በኤኮኖሚ በሳይንስ በባህልና በወታደራዊ ትብብር መስኮች አሁንም የዳበረ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግረዋል። የ74 ዓመቱ ሳልሳዊ ቻርልስ የጀርመን ጉብኝት እስከ ነገ ይቀጥላል።በቀደመው እቅድ ቻርልስ ንጉስ ከሆኑ ወዲህ የውጭ ጉብኝታቸውን በፈረንሳይ ለመጀመር ነበር ያሰቡት።

König Charles Rede Bundestag
ምስል Wolfgang Kumm/dpa/picture alliance

የብሪታንያው ንጉስ ሳልሳዊ ቻርልስ የጀርመን ጉብኝት

This browser does not support the audio element.

ጀርመንን በመጎብኘት ያሉት አዲሱ የብሪታንያ ንጉስ ሳልሳዊ ቻርልስ ብዙ ዘመናትን ያስቀጠረው የብሪታንያና የጀርመን ጥብቅ ግንኙነት ዛሬም በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን አስታወቁ። ንጉስ ሳልሳዊ ቻርልስ ዛሬ በጀርመን ፓርላማ ቡንደስታግ ባሰሙት ንግግር ሁለቱ ሀገራት በኤኮኖሚ በሳይንስ በባህል እና በወታደራዊ ትብብር መስኮች አሁንም የዳበረ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ትናንት የተጀመረው የ74 ዓመቱ ሳልሳዊ ቻርልስ የጀርመን ጉብኝት እስከ ነገም ይቀጥላል። በቀደመው እቅድ ሳልሳዊ ቻርልስ ንጉስ ከሆኑ ወዲህ የውጭ ጉብኝታቸውን በፈረንሳይ ለመጀመር ነበር ያሰቡት። ሆኖም ፈረንሳይን ሊጎበኙ ካሰቡበት ጊዜ ጋር  በተገጣጠመው የፈረንሳዩ ተቃውሞ ምክንያት የውጭ ጉብኝታቸውን በጀርመን ጀምረዋል። ስለ ጀርመን ጉብኝታቸው የበርሊኑን ዘጋቢያችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። 
ኂሩት መለሰ 
ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW