1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪክስ የሦስት ቀናት ጉባኤ ዛሬ ጆሃንስበርግ ላይ ጀመረ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 16 2015

15ኛዉ የብሪክስ የሦስት ቀናት ጉባኤ ዛሬ ደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ ላይ ዛሬ በይፍ ጀመረ። ብራዚል፣ ሩስያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃን ያቀፈዉ የብሪክስ ጉባኤ አዳራሽ ዩክሬንን የወረረችዉን ሩስያን አስመልክቶ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የመብት ተሟጋቾች ከባድ ተቃዉሞ ገጥሞታል።

Südafrika BRICS-Gipfel
ምስል Jerome Delay/AP Photo/picture alliance

15ኛዉ የብሪክስ የሦስት ቀናት ጉባኤ ዛሬ ደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ ላይ ዛሬ በይፍ ጀመረ። ብራዚል፣ ሩስያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃን ያቀፈዉ የብሪክስ ጉባኤ አዳራሽ ዩክሬንን የወረረችዉን ሩስያን አስመልክቶ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የመብት ተሟጋቾች ከባድ ተቃዉሞ ገጥሞታል።  

ብራዚል፣ ሩስያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃን ያካተተዉ እና ብሪክስ በመባል የሚታወቀዉ የአምስት ሃገራት ቡድን፤ ዛሬ ደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ ላይ የሦስት ቀናት ጉባዔውን ጀመረ። ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማሳየት ላይ የሚገኙት የአምስቱ ሃገራት ስብስብ፤ የአውሮጳ እና የዩናይትድ ስቴትስን ግዙፍ ተፅዕኖ ለመቋቋም እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን እየሰራ ያለ ቡድን መሆኑ ተመልክቷል። ዛሬ ጆሃንስበርግ ላይ የጀመረዉ 15ኛዉ የብሪክስ ጉባኤ በአባልነት እንቀላቀል ሲሉ ጥያቄ ያቀረቡ ሃገራትን ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጥም ይጠበቃል። ለብሪክስ የአባልነት ጥያቄ ካቀረቡ ዋንኛ ሃገራት መካከል ሳውዲ አረቢያ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ኢራን፣ ቱርክ፣ ግብጽ እና አልጀሪያ  ይገኙበታል። ኢትዮጵያም ለብሪክስ የአባልነት ጥያቄ ማቅረብዋ አይዘነጋም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፤ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የመብት አቀንቃኞች፤ የዩክሬንን ሰንደቅ ዓላማን በመያዝ ዛሬ ጆሃንስበርግ ከተማ ውስጥ በሚገኘዉ በጉባኤዉ አዳራሽ ፊት ለፊት ተቃዉሟቸዉን አሰምተዋል። በጉባኤዉ ላይ ከሩስያዉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በስተቀር የቡድኑ አባል ሃገራት ፕሬዚዳንቶች ተካፋይ ናቸዉ። ባለፈዉ መጋቢት ወር የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ሩስያ ዩክሬይንን መዉረሯን ተከትሎ የእስር ትዕዛዝ ያወጣባቸዉ ቭላድሚር ፑቲን፤ በጉባኤዉ ላይ እንዲወክሏቸዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭን መላካቸዉ ተነግሯል። 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW