የብራስልስ የፀጥታ ሁኔታ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 20 2008ማስታወቂያ
ዛቫቴም አዉሮፕላን ማረፊያ በደረሰው የሽብር ጥቃት እጁ እንዳለበት የተጠረጠው እና በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ሶስተኛው ሰውም በቂ ማስረጃ አልተገኘበትም በሚል ተለቋል። እንደ የብራስልስ ከንቲባ ከሆነ፣ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ፋይሳል ሼፉ መለቀቅ አልነበረበትም። ከንቲባው ምንም እንኳን ፋይሳል ሼፉ ከአይሮፕላን ማረፊያው ጥቃት ጋር በተያያዘ ተይዞ መቆየት ባይችልም፤ ግለሰቡ ከወንጀል ንጹህ እንዳልሆነ ዛሬ ለሀገራቸው የመገናኛ ብዙኃን ገልፀዋል። ቤልጂየም አሁንም ተጠርጣሪዎችን እያሰሰች እና እየመረመረች ትገኛለች። ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የብራስልስ አዉሮፕላን ማረፊያም ስራ አልጀመረም።
ገበያው ንጉሴ
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ