የብሬግዚት ቀነ ቀጠሮ ተራዘመ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 3 2011ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ኅብረት ልዩ ጉባዔ ብሪታንያ ከኅብረቱ የምትወጣበትን እንደአዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር የፊታችን ጥቅምት 31 ድረስ በግጋሚ እንዲወሰን ትናንት ባካሄደዉ ልዩ ጉባዔ ወስኖአል። ኅብረቱ ባላፈዉ ባካሄደዉ የመሪዎች ጉባዔ እስከዛሬ ማለት መጋቢት ሦስት ድረስ የመዉጫ ስምምነቱን ብሪታንያ ካላፀደቀች ፤ በነገዉ እለት ከኅብረቱ ያለምንንም ሥምምነት እንድትወጣ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም አቅላይ ሚኒስትር ሜይ ግን ስምምነቱ በፓርላማቸዉ ባለማለፉ ሃገራቸዉ እንዲሁ ያለስምምነት እንዳትወጣ ለመከላከል ጊዜዉ ዳግም እንዲራዘም በጠየቁት መሰረት ነዉ ትናንት ኅብረቱ ባካሄደዉ ልዩ ጉባዔ የመዉጫዉ ቀን እንዲራዘም የተወሰነዉ ። የብረስልሱ ወኪላችን ተጨማሪ ዘገባ አለዉ።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ