የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት መቃጠል
ቅዳሜ፣ መጋቢት 13 2006ማስታወቂያ
የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት የቃጠሎ መንስኤ ለጊዜው በዝርዝር ባይገለፅም በማተሚያ ቤቱ ላይ እሳቱ የተነሳው ከቀኑ 9 ሠዓት ተኩል ግድም እንደሆነ የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ከአካባቢው ነዋሪዎች ያገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ ገልፆልናል። እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተነግሯል። የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት በዕድሜ ጠገብነቱ እና ግዝፈቱ በሀገሪቱ ብቸኛው የማተሚያ ቤት እንደሆነ ይጠቀሳል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ