1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መከልከል

ረቡዕ፣ ጥር 29 2016

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ትናንት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ መደረጉን ቤተ ክርስትያኗ አስታወቀች። ቤተ ክርስትያኗ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ "ወደ አገር እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው" ጥሪ ብታደርግም ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲመለሱ ተደርገዋል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት
ቤተ ክርስትያኗ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ "ወደ አገር እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው" ጥሪ ብታደርግም ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲመለሱ መደረጋቸው ተገልጿልምስል Seyoum Hailu/DW

የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መከልከል

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ትናንት ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ አማሪካ እንዲመለሱ መደረጉን ቤተ ክርስትያኗ አስታወቀች። 

ቤተ ክርስትያኗ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ "ወደ አገር እንዲገቡ  እንዲፈቀድላቸው እንዲደርግ" ጥሪ ብታደርግም ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉ ተሰምቷል። 

የቤተ ክርስትያኗ የመንበረ ፓትርያርክ የሕዝብ ግንኙነት የሕትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ መምህር ዶክተር አካለወልድ ተሰማ ዛሬ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ትናንት ወደ አገር እንዳይገቡ መከልከላቸውን አረጋግጠው "ቋሚ ሲኖዶስ በዛሬ ስብሰባው ይሄው ጉዳይ ትነስቶ ውይይት ተደርጎበታል" ሲሉ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።

"ልክ ነው እንዳይገቡ ተደርጓል" 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ እና በዩናይትድ ስቴትስ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ   ለአገልግሎት ከቆዩበት አሜሪካ ወደ አገር እንዳይገቡ መከልከላቸውን ቤተ ክርስትያኗ አስታውቃ ነበር።

 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን መግለጫ

ትናንት ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያው ይገኙ እንደነበር ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በአየር መንገድ አቀባበል ለማድረግ በተገኘበት ወቅት ማረጋገጡ ተጠቅሷል። "የሚመለከተው የመንግስት አካል የቤተክርስቲያናችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ  መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አገር እንዲገቡ  እንዲፈቀድላቸው እንዲደርግ" ስትል ቤተክርስቲያኗ ጥሪ ብታደርግም ሳይሳካ መቅረቱንና እንዲመለሱ መደረጉን የመንበረ ፓትርያርክ የሕዝብ ግንኙነት፣

የሕትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ መምህር ዶክተር አካለወልድ ተሰማ በተለይም ለዶቼ ቬለ ዛሬ ምላሽ ሰጥተዋል።
አሁን ልገልጽልህ የምችለው "ልክ ነው ሲመለሱ ወደ አገር እንዳይገቡ እንደተከለከሉ እና ወደመጡበት ወደ ሀገረ ስብከታቸው እንደተመለሱ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አሜሪካ ያቀኑት የጥምቀት በዓልን ለማክበር እንደነበር ተገልጿል። ምስል Solomon Muchie/DW

ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ተወያይቷል

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ይህ ክስተት ከተፈጠረ በኋላ ከማሕበረ - ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን "ወደመጣሁበት ወደ አሜሪካ መለሱኝ" በማለት ገልፀዋል።

 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የመንግሥት ውዝግብ

የጥምቀት በዓል አከባበርን እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በዚህ ወር መጀመርያ አካባቢ መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቤተ ክርስትያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ኮበለሉ የሚባለው መረጃ ሐሰት እንደሆነ በወቅቱ ገልፀው ነበር። ዋና ሥራ አስኪያ "በደል ይቁም፣ ሰላም ከሀገር እስከ ሀገር ይስፈን" የሚል ጥሪም አድርገው ነበር።  ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ አሜሪካ ስለመድረስ አለመድረሳቸው መምህር ዶክተር አካለወልድን የጠየቅናቸው ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ነበር። 

ሰለሞን ሙጬ

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW