1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቦረናን ድርቅ ለመቋቋም ድጋፍ እየተደረገ ነዉ ተባለ

ዓርብ፣ የካቲት 17 2015

በደቡብ ኦሮሚያ በተሌም በቦረና ዞን ድርቅ ያስከተለውን ቀውስ ለመቋቋም የተለያዩ ድጋፎችን ለማዳረስ ጥረቶች መቀጠላቸውን መንግስት አስታወቀ፡፡ የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ከድር በተሌም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በተራዘመው ድርቅ የተረጂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፡፡

Äthiopien I Nationale Regionalregierung von Oromia Bussa Gonfa Hauptgeschäftsstelle
የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋምስል Seyoum Getu/DW

በተራዘመው ድርቅ የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ ነዉ

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ኦሮሚያ በተሌም በቦረና ዞን ድርቅ ያስከተለውን ቀውስ ለመቋቋም የተለያዩ ድጋፎችን ለማዳረስ ጥረቶች መቀጠላቸውን መንግስት አስታወቀ፡፡ የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ከድር በተሌም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በተራዘመው ድርቅ የተረጂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፡፡

እንደ አቶ ሙስጠፋ ማብራሪያ በተለይም በቦረና ከብቶችን ያወደመው ድርቅ ህብረተሰቡን ለባሰ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ቢዳርግም፡ በምግብ እጥረት ምክኒያት የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው መባሉን ግን አስተባብለውታል፡፡

በደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ከፍቶ የቀጠለው ድርቅ ክፉኛ ከጎዳቸው አከባቢዎች በከፍተናኛ የከብት እርባታ የሚታወቀው የኦሮሚያ ክልሉ የቦረና ዞን ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚሁ ክልል ብቻ የወረዳዎች ስፋት ይለያይ እንጂ ምስራቅ አፍሪቃ ላይ የተስፋፋው ድርቅ በኦሮሚያ ክልል ብቻ 10 ዞኖችን አጥቅቷል፡፡ ይህንኑን የተስፋፋውን ድርቅ ለመቋቋም መንግስት የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶችንም ጭምር በማስተባበር በቢሊየን የሚቆጠር ድጋፎችን በማስተባበር ለተጎጂዎች እያደረሰ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ከድር ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋምስል Seyoum Getu/DW

እንደ ሃላፊው ማብራሪያ ድርቁ በከፋ ደረጃ የጎዳው ለአምስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ አልባ ሆነው የቀጠሉት እንደ ቦረና ያሉ አከባቢዎችን ነው፡፡ በተለይም በቅርብ ጊዜያት ይህ የተራዘመው ድርቅ መባባሱ የተረጂዎችንም ቁጥር ከፍ አድርጓል፡፡

እንደ አቶ ሙስጠፋ ማብራሪያ በተለይም በቦረና ከብቶችን ያወደመው ድርቅ ህብረተሰቡን ለባሰ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ዳርጎታል፡፡ ኃላፊው በምግብ እጥረት ምክኒያት የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው መባሉን ግን አስተባብለውታል፡፡

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW