1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቦሮ ዴሞክራክ ፓርቲ የምርጫ ምልክቱን እና ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 25 2013

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ዛሬ በአሶሳ ከተማ የምርጫ ምልክቱን እና ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ። ፓርቲው መስከረም 2012 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ይሳተፋል። ፓርቲው ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤት 26 ዕጩዎችን ማቅረቡ ተገልጿል።

Äthiopien Addis Abeba | Boro-Partei, EInweihungstreffen
ምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ዛሬ በአሶሳ ከተማ የምርጫ ምልክቱን እና ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ። ፓርቲው በመጪው ምርጫ  የሚያሸንፍ ከሆነ የክልሉን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅና የህግ የበላይነትን  ማስከበር፣ በህዝቦች መካከል የተፈጠሩ አንድነትን የሚያሻክሩ ችግር የመቅረፍ ተግባርን እንደሚያከናውን አመልክተዋል። የክልሉን  የተለያዩ ህጎችን እንደሚያሻሽል እና አማራጭ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርግም ፓርቲው ገልጿል። በመተከል ዞን የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንና እጅግ እንደሚያሳስባቸው የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ አመንቴ ግሺ  ተናግረዋል። 

የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ዛሬ የለህዝብ ተወካዩች እና ክልል ምክር ቤት ያቀረባቸውን ዕጩዎች እና የፓርቲውን ፖሊሲዎችን አስተዋውቋል።  የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አመንቴ ግሺ ፓርቲያቸው በክልሉ እጅግ የተሰንራፍ ያሉትን የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የተፈጥሮ ሀብት ምዝበራ እና የዴሞከራሲ እጦት እንዲሁም በክልል ደረጃ በዜጎች የሚነሱ የፖለቲካ አካታችነት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እንደሚሰራ ተናግረዋል። የቦሮ ዴሞክራክ ፓርቲ ከሌሎችም በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ክልላዊና ሀገራዊ ፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል። ፓርቲው በክል ውስጥ በሚስተዋለው ጸጥታ ችግር ምክንያት እጩዎች በሚፈለገውን ያህል ማስመዝገብ አለመቻሉን አክለዋል። 

የዘንድሮ ምርጫ "የህልውና ምርጫ ነው" ብሎ የሚያሚነው የቦሮ ዴሞክራክ ፓርቲ የዜጎች በክልሉ በተለይም በመተከል ዞን በረዥም ጊዜ የጸጥታ ችግር ውስጥ መቆየታቸውን ገልጿል። የጸጥታ ችግሩ  ዘላቂ መፍትሄ እንደሚሻ እና ምርጫም ሰላማዊ ሆኖ እንዲካሄድ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ለአካባቢው ኮማንድ ፖስት ጥያቄ ማቅረቡን ፓርቲው አመልክቷል።  የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ተሰማ በዘንድሮ ምርጫ ካሸነፉ  የዜጎችን ደህንነት ከመጠበቅ አንስቶ ውዝፍ ያሉትን የፖለቲካና ማህበራዊ ቅራኔዎች ለመፍታት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በክልሉ በኢንቨስትመንትና የፖለቲካ ተሳትፎም ፍትሀዊነት እንዲሰፍን ፓርቲው ጥረት እንደሚያረግም አክለዋል። 

የቦሮ ዴሞክራክ ፓርቲ በመስከረም 2012 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫይሳተፍል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፓርቲው ለህዝብ ተወካዩች እና ለክልል ምክር ቤት 26 ዕጩዎችን ማቅረቡ ተገልጿል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ታምራት ዲንሳ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW