የቦሮ ዴሞክራክ ፓርቲ
ቅዳሜ፣ የካቲት 20 2013
ከዚህ ቀደም የፓርቲውን ሊቀመንበር ጨምሮ አመራሮቹ በመታሰራቸው ፓርቲው ለምርጫ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ላይ ተዕጽኖ ማሳደሩን ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ የፓርቲው ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዩሐንስ ተሰማም ትናንት ተለቀዋል፡፡ የቦዴፓ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መብራቱ አለሙ ፓርቲአቸው በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ እና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ዕውቅና ያለው መሆኑን ገልጸው በአመራሩ ላይ የሚደረገው ወከባ መቆም አለበት ሲሉ አስረድተዋል።
የተቋዋሚ የፖለቲካ ፓርዎች የሚያቀርቡትን ቅሬታም በተመለከተ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም ሙሐመድ ለDW እንደተናሩት በክልል ውስጥ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ በነበሩት ግጭቶች ውስጥ የተሳተፉ ስለመኖቸራው ገልጸው የፓለቲካ ፓርቲም ሆነ ግለሰብ በወንጀል ድርጊት የሚሳተፍ ከሆነ ህግ የማስከበር ስራ እንሰራንል ብለዋል፡፡
የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ(ቦዴፓ) በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ካሉት ሶስት የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን አመራሮቹ በተለያዩ ጊዜያት ሲታሰሩ ስለመቆየታቸው ፓርቲው አስታውቋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር እና የፓለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ለወራት በእስር ላይ የቆዩ ሲሆን የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ አመንቴ ግሽ ሀሙስ ዕለት ከእስር ተፈተዋል፡፡ ከፓርቲው ምስረታ ጀምሮ የፓርቲ አመራሮች በተደጋጋሚ መታሰራቸውን አክለው መንግሰት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፓለተካ ፓርቲዎችን ማወያየት እንዳበለትም ጠቁመዋል፡፡ መጪው ምርጫም ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ከሌሎች ተቋዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት የፓርቲው ዕቅድ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከሰባት ወራት በላይ በአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት የቆዩትና ሀሙስ ረፋዱ ላይ የተለቀቀሉት የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ኃላፊ አቶ አመንቴ ግሺ ባለፈው ዓመት 3 ጊዜ መታሰራቸውን ተናግረዋል፡፡ የፓርቲያቸው የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዩሐንስ ተሰማም ዓርብ ዕለት መፈታታቸውን አክልዋል፡፡
የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ በሰጡን ማብራሪያ በክልሉ ህግን አክብረው በማይሰሩ ግልሰቦችም ሆነ ፓርዎች ከዚህ ቀደም በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጋቸውን ተናግረው የታሰሩ ሰዎች የፓለቲካ ፓርቲ አባል ወይም መሪ በመሆናቸው አይደለም ብለዋል፡፡ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ ትግል ትተው ህዝብን ወደ ማሳመጽ ስራ ከተሰማሩ የክልሉ መንግስት ተከታትሎ ህግን እንደሚያስከብርም አብራርተዋል፡፡
የቦሮ ዲሞክራክ ፓርቲ በመስከርም 2012 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን ዘንደሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ይሳተፋል ተብሎም ይጠበቃል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ልደት አበበ