የቦዴፓ የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ
ረቡዕ፣ የካቲት 26 2017
የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ያጸደቃቸውን የምክር ቤት ተወካዮች ብዛት ለመወሰን የወጣውን አዋጅና የተሻሻለው ሕገ-መንግስት የሕዝብ ብዛትን መሰረት ያላደረገ እና ኢ-ፍትሀዊ ነው ሲል አቤቱታ አቀረበ ። ሦስት የፓርቲው የምክር ቤት አባላት የሕግ መንግስት ትርጉም እንዲሰጥበት ለሕግ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የካቲት 24 ቀን፣2017 ዓ፣ም አቤቱታ ማቅረባቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አመንቴ ግሺ አመልክተዋል፡፡
የምክርቤቱ የተወካዮች ብዛት ለመወሰን የጸደቀው አዋጅ ብዙ ህዝብ ቁጥር ያለው መተከል ዞን ህዝብ ቁጥር እያለው አነስተኛ ውክልና እንደተሰጠው አንስተዋል፡፡ አቤቱታውም በጉዳዩ ላይ የህገ መንግስት ትርጉም እንዲሰጠውና ተግባራዊ እንዳይሆን ነው፡፡
የጸደቀው አዋጅ ኢ-ፍትሐዊና አድሎአዊ አሠራርን የተከተለ ነው
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ገባኤውን ባካደቤትበት ወቅት የየእርከኑን ምክር ቤት ተወካዩች ብዛት ለመወሰን የወጣ አዋጅና የክልሉን ህገ መንግስት እንደገኛ ለማሻሻል የቀረበው ማሻሻያ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት የሆኑት ሦስት የቦሮ ዶሞክራሲያ ፓርቲ አባላት አዋጁ የህዝቦችን እኩልነትና አንድትን የምንድና ህገምግስትን የምቃረኑ ናቸው በማለት መቃወማቸውን አመልክተዋል፡፡ የምክር ቤት ተወካዮች ብዛትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ በስራ ላይ የነበረውን የምክር ቤት መቀመጫ ከ99 ወደ 165 ማሻሻሉን የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አመንቴ ግሺ ተናግረዋል፡፡
የተሻሻለው የተወካዮች ቁጥርም በክልሉ ውስጥ የሚገኘውን ዞኖችን አንድ ልዩ ወረዳ ህዝብ ብዛትን ማእከል ያላደረገ እና በወረዳ ብዛት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ህገ መንግስት የጣሰ አሰራር ነው በማለት ከትናንት በስቲያ ለህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ገባኤ አቤቱታ ማቅረባቸውን አመልክተዋል፡፡ በተሻሻለው የክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 48 መሰረት የክልሉ ምክር ቤት አባላት ቁጥር የህዝብ ቁጥርን መሰረት ያደረገ ይሆናል ሲል እንደሚደነግግ ተገልጸዋል፡፡
ክልሎች የሕዝብ ተወካዮችና ክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል የመከለል ስልጣን የላቸውም
የክልል ምክር ቤት አባላት የሆኑት 3ቱ የቦሮ ፓርቲ አመራሮችን ካቀረቡት አቤቱታ ለመረዳት እንደተቻለው የጸደቀው አዋጅና የህግ መንግስት ማሻሻያ ስርዓት የተወሰኑ ነባር የምርጫ ክልልሎች ያፈረሰና አዲስ ምርጫ ክልሎችን ደግሞ ያቋቋመ በመሆኑ የሀገሪቱ ህገ መንግስት የጣሰና አድሎአዊ ሲል ገልጾታል፡፡ በተጨማሪም የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ አመንቴ ግሺ አሰራሩ በየፌደሬሽን ምክር ቤትና ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ በ1987 የተቃቋሙ 3 ምርጫ ክልሎችን በማፍረስ አዳዲስ 5 ምርጫ ክልሎችን በማቋቋም የተቋማቱን ስልጣን የተጋፋ ነው ብሏል፡፡ የህዝብ ተወካዮችን የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል አከላለል በተመለከተ ክልሎች ስልጣን እንደደላቸው የገለጸው ቦሮ ፓርቲ የተቋቋሙት የምርጫ ክልሎች ህግ መንግስትን የጣሱ አሰራሮች በመሆናቸው የጸደቁ አዋጆች ተግባራዊ እንዳይሆኑ አቤቱታ ማቅረቡን አስረድተዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የካቲት 10-11/2017 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤው የክልሉን ሕገ-መንግስት እንደገና ለማሻሻልና የወጣን አዋጅና የምክር ቤቱን ተወካዮች ብዛት ለመወሰን የቀረበውን አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ማጽደቁን በወቅቱ አመልክቷል፡፡
ነጋሣ ደሳለኝ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ታምራት ዲንሳ