1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቪክቷር ኢንጋብሬ ክስ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 17 2005

የሩዋንዳ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የወይዘሮ የቪክትዋር ኢንጋብሬ ክስ ከትናንት ጀምሮ በመዲና ኪጋሊ መደመጥ ጀምሯል። ኢንጋብሬ ባለፈው ጥቅምት በፀረ መንግስት እንቅስቃሴ ተከሰው የስምንት አመት እስራት ተበይኖባቸዋል። የኢንጋብሬ ጠበቆች ይግባኝ ጠይቀዋል። የሀገሪቱ አቃቢ ሕግም ያለፈው ቅጣት መክበድ አለበት በማለት ይሟገታል።

Rwandan opposition leader Victoire Ingabire wears handcuffs, as she listens to the judge during the her trial in Kigali, Rwanda Monday, Sept. 5, 2011. Ingabire, an outspoken critic of President Paul Kagamea's regime, is charged with allegations of providing financial support to a terrorist group, causing state security and formenting ethnic divisions. (ddp images/AP Photo/Shant Fabricatorian).
Victoire Ingabire Oppositionsführerin Ruandaምስል AP

የሩዋንዳ መንግስት ተቃዋሚ በምህፃሩ የ FDU ፓርቲ መሪ -ቪክቶሬ ኢንጋብሬ  ባለፈው ጥቅምት አጋማሽ ነበር የስምንት አመት እስራት የተበየነባቸው። ይህም በአሸባሪነት እና እኢአ በ 1994 ሩዋንዳ ውስጥ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል አጣጥለዋል በሚል ክስ ነበር።  

የሰብዓዊ መብት ተሟጋጁ ድርጅት- አምንስቲ ኢንተርናሽናል ፤ትናንት ባወጣው መግለጫ  የቪክቶሬ ኢንጋብሬ ክስ አለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ እንዲታይ ጠይቋል።

ቪክቶሬ ኢንጋብሬምስል AFP/Getty Images

የክስ ማድመጡ ሂደት በርካታ ችግሮችን ማረሚያ ይሆናል ነው ያሉት በርሊን የሚገኘው የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ተወካይ ሱዛነ ባልደን፤ ምን አይነት ዕርማቶች ማለታቸው እንደሆነ ያስረዳሉ። « በአጠቃላይ በ የቪክትዋር ኢንጋብሬ ላይ የተመሰረተው ክስ በሁለት ይከፈላል ማለት እንችላለን። አንዱ በምርጫ  ዘመቻ ወቅት ካደረጉት ንግግር ጋ የተያያዘ ሲሆን ሌላው ከሽብርተኝነት ጋ የተያያዘ ነው። የዳኞቹን ባህሪ በተመለከተ በርካታ ችግሮች አይተናል።  ዳኞቹ በተከሳሽ ጠበቆች ላይ ከፍተኛ ጫና ሲፈፅሙ ተስተውሏል። ቪክቶሬ ኢንጋብሬም ይሁኑ ለሳቸው በጥብቅና የቆሙት በዳኞቹ በተደጋጋሚ ንግግራቸው እየተቋረጠ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ነበር። ሌላ እንዱ ትልቅ ችግር  በአቃቢ ህጉ የቀረበው ማስረጃ  በዳኞቹ ዘንድ የነበረው ተቀባይነት በተከሳሽ ጠበቆች  ከቀረበው  የተለየ ነበር።»

ጠበቆቹ በሚያቀርቡት ማስረጃ ላይ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳ በአቃቢ ህጉ በኩል ሊነሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች አለመነሳታቸውን  ሱዛነ ባልደን እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ። የቪክትዋር ኢንጋብሬን ይግባኝ ከትናንት ጀምሮ የሚመለከተው ፍርድ ቤትም ካለፈው ፍርድ ቤት ጋ ተመሳሳይ ነው ። በርግጥ የአቋም ለውጥ ይኖራል ብለው ሱዛነ ባልደን ይጠብቁ ይሆን?

ኪጋሊምስል cc-by-sa/SteveRwanda

«አሁን እኛ የምንጠብቀው የሩዋንዳ ባለስልጣናት በተለይም የፍትህ ሹማምንቶች ለቪክትዋር ኢንጋብሬ የአለም አቀፉን ደረጃ የጠበቀ የፍትህ አሰጣጥ እንዲያመቻቹ ነው። እንደኛ አመለካከት ከንግግሩ ጋ የተያያዘው ክስ መሰረተ ቢስ ነው። ምክንያቱም የኛ ታዛቢዎች እንደተከታተሉት ኢንጋብሬ ያደረጉት ንግግር  የሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት የሚያንፀባርቅ ብቻ ነው። »

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት እና የፖለቲከኛዋ ደጋፊዎች እንደሚመኙት የክስ ማድመጡ ሂደት በገለልተኝነት መካከድ አለበት። ይህ ካልሆነ ግን እንደ ሱዛነ ባልደን፤የአለም አቀፉ ወይንም የውጭ ተፅዕኖ ፍታዊ ፍርድ ለመስጠት መፍትሄ ሊሆን ይችላል።

« እንደዚህ አይነት ክሶች በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ወይንም በአለም አቀፉ ድርጅቶች ክትትል ቢደረግባቸው በጣም አስፈላጊ ነው። ሩዋንዳ ሁሉንም አይነት አለም አቀፍ ስምምነቶች ፈርማለች። እና በተለይም የቪክትዋር ኢንጋብሬ ክስ ከፍተኛ የአለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቱ በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም የቪክቶሬ ኢንጋብሬ ጉዳይ በኛ አመለካከት በፖለቲካም በህጋዊም ገፅታው በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው።  ሩዋንዳ እንደዚህ አይነት ከፍተኛ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ብቻዋን የመወጣት አቅም እንዳላት የሚረጋገጥበት ጉዳይ ነው።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW