1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የተለመደዉ» የኢሕአዴግ መግለጫ 

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 12 2010

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አሁን በአገሪቱ ዉስጥ ለተፈጠረዉ የፖለቲካ ቀዉስ ተጠያቂዉ ድርጅቱ ራሱ መሆኑን ትላንት በመግለጫዉ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት ሰዎች ከሁለት ዓመት በፊት መንግሥት «የወጣቱ ተቃዉሞ ሥራ አጥነትና የራሴ የመልካም አስተዳደር ችግር ነዉ» ካለዉ የተለየ ነገር የለዉም በማለት ይከራከራሉ። 

12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

Reaction from FB + Whatsapp Discussion - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አሁን አገሪቱ ዉስጥ «እየተከሰቱ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በዋነኛነት የድርጅታችን አመራር ያሳየው ድክመት የፈጠራቸው» ናቸዉ ሲል ትላንት ይፋ ባደረገዉ መግለጫ አሳዉቋል። መግለጫዉ አገሪቱን ወደ አስጊ ሁኔታ ዉስጥ እንድትገባ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ድክመት ትልቅ ሚና መጫወቱንም አክሎበታል።

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ እና የሚታዘቡ ዜጎች ድክመቱን እና ተጠያቂነቱን በይፋ ማመን አንድ ነገር ሆኖ የፖለቲካ ቀዉሱ ለብዙዎች መሞት፣ መቁሰልና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ተጣርተዉ ለፍትህ እንዲቀርቡ እንዲደረግ ይጠይቃሉ።

ይህን አስመልክቶ በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ገፅ እና ዋትስአፕ ላይ አስተያየታቸዉን ከሰጡት መካከል፤ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባወጣዉ መግለጫ የፖለቲካ ቀዉሱ የራሳቸዉ ችግር የወለደዉ መሆኑን ማመናቸዉ ትልቅ ነገር ነዉ ያሉ አሉ። በተቃራን ግን አንድንዶቹ ይህ መግለጫ ሳይሆን «ማላገጫ» ነዉ ብለዉታል። ገሚሶቹ ደግሞ «አሳፋሪ መግለጫ» ሲሉ ትችታቸዉን ሰንዝረዋል።

ቤዛ በዉቀቱ ብንያም በፌስቡክ ፤ ኢህአዴግ «ትላንት ከዜሮ ተነስቶ የሚያስደምም ታሪክ የሰራ የአገራችን የቁርጥ ቀን ዴሞክራሲያዊ ድርጅት» ስትል፤ ለቤዛ መልስ የሰጣት ታደሰ ዳዲ  ደግሞ «ኢህድግ የሰላም አለኝታ ቢሆን ኖሮ በገዛ ወገኖቹ ላይ ለሰላማዊ ጥያቄ በተወጣ ቁጥር ወንድሞቹን ባልገደለ» ነበር የሚል አስተያየቱን ጽፏል።

ኢሕአዴግ የሰዉን ህይወት እየቀጠፈ ያለ እንዲህ ጥፋቱን ካመነ፣ ስልጣን ለቆ ብሔራዊ ምርጫ መጥራት አለበትም ሲሉ በዋትስአፕ አስተያየታቸዉን  የላኩልን አሉ።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW