1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ - ዘመቻ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 16 2018

በተባበሩት መንግስታት ሴት ድርጅቶች፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚቃወም ዘመቻ ጀመሩ። ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2024 ዓመት ብቻ ወደ 50,000 የሚሆኑ ሴቶች እና ታዳጊ ሴት ልጆች በወዳጆቻቸዉ አልያም በቤተሰብ አባላት ተገድለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ መረጃ አዉጥቷል።

በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ -ዘመቻ 
በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ -ዘመቻ ምስል፦ Uli Deck/dpa/picture alliance

የተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ -ዘመቻ 

በተባበሩት መንግስታት ሴት ድርጅቶች፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚቃወም ዘመቻ ጀመሩ። ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2024 ዓመት ብቻ ወደ 50,000 የሚሆኑ ሴቶች እና ታዳጊ ሴት ልጆች በወዳጆቻቸዉ አልያም በቤተሰብ አባላት ተገድለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ መረጃ አዉጥቷል። የመንግሥታቱ ድርጅት አሳሳቢ ያለዉ በሴቶች ላይ የሚፈፀም ግድያ በያዝነዉ ዓመትም ቁጥሩ አልቀነሰም አልያም ምንም አይነት ለውጥ አልመጣም ብሏል።
ፖለቲከኞች በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የተለያዩ ጥቃቶችን ለመዋጋት የበለጠ እንዲሰሩ በተባበሩት መንግስታት የሴት ድርጅቶች ጥሪ ቀርቧል። የ"ብርቱካን ዓለም" የተሰኘዉ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃቶችን ለማስቆም የተጀመረዉ ዘመቻ ሴቶች እና ልጃገረዶች፤ በህዝባዊ እና ዲጂታል ቦታዎች ላይ በተሻለ ሁኔታ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል  አጽንዖትም ሰጥቷል። ለ16 ቀናት በሚዘልቀዉ በዚህ ዘመቻ በርካታ የመዝናኛ ቦታዎች  እና ተቋማት ዉስጥ ብርቱካናማ መብራቶችን ወይም "ጥቃት ይቁም" የሚል ጽሁፎችን  በማስቀመጥ ዘመቻዉ ለህዝብ እንዲታይ ተደርጓል። ዛሬ በጀመረዉ በዚህ ሴቶች ላይ ጥቃት ይቁም ዘመቻ ላይ የጀርመን ፌዴራል ሚኒስትሮች፣ አብያተ ክርስቲያናት እና የጀርመን እግር ኳስ ማህበር ተሳታፊ ናቸዉ። የመንግሥታቱ ድርጅት በዛሬዋ እለት ማለት በጎርጎረሳዉያኑ ኅዳር 25 ቀን 1999 በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዲቆሙ ጥሪ የሚደረግበት ቀን ብሎ መታወጁ ይታወቃል።    
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW