1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ የሰብዓዊና የአስቸኳይ ዕርዳታ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ጉብኝት  

ረቡዕ፣ ሐምሌ 28 2013

በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የተመድ የሰብዓዊና የአስቸኳይ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትዝ በጎበኙዋቸው የትግራይ አከባቢዎች የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ መፈጠሩን ተናግረዋል።ትናንት የ6 ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው የተመለሱት ግሪፊትዝ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የእርዳታ ቁሳቁሶቹን ለተረጂዎች የማድረሱ ስራ እንዲፈጥን መስማማታቸውም ተነግሯል።

Schweiz Glion | Treffen zu Gefangenenaustausch mit der Schweiz
ምስል Denis Balibouse/Reuters

«በትግራይ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ተፈጥሯል»

This browser does not support the audio element.

 

 በትግራይ ከ5 ሚሊየን የሚበልጥ ህዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የተመድ አስታወቀ።ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የተመድ የሰብዓዊና የአስቸኳይ ዕርዳታ አስተባባሪ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ኦቻ ሃላፊ  ማርቲን ግሪፊትዝ በትግራይ በጎበኙዋቸው አከባቢዎች የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ መፈጠሩን ተናግረዋል።ትናንት የስድስት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው የተመለሱት ግሪፊትዝ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር አደረግን ባሉት ፍሬያማ ውይይት የእርዳታ ቁሳቁሶቹን ለተረጂዎች የማድረሱ ስራ እንዲፈጥን መስማማታቸውም ተነግሯል።ስዩም ጌቱ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW