የመሪዎች መልዕክት
ረቡዕ፣ መስከረም 16 2011
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ፤ የኤርትራ እና የጀቡቲ መሪዎች በየሐገራቱ መሐል የቆየ ጠብ፤ ግጭታቸዉን አስወግደዉ ሠላም ለማዉረድ በቅርቡ መስማማታቸዉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ በድጋሚ አወደሱ።ጉተሬሽ ትናንት የድርጅታቸዉን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት ከአፍሪቃ ቀንድ የበጎ ተስፋ ነፋስ እየነፈሰ ነዉ።የዓለም አቀፉ ድርጅት ጉባኤ ከጉባኤዉ በፊት እንደተጠበቀዉ ለዩናይትድ ስቴትስ እና ለኢራን መሪዎች የመወዛገቢያ መድረክ ሆኗል።የተናጥል ወይም የግለኝነት አስተሳሰብ የሚያራምዱት የዩናያትድ ስቴትስ መሪ ዶናልድ ትራምፕ በጋራ መርሕ ከሚያምኑት ከሌሎች ሐገራት መሪዎች ትችት አላመለጡምም።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ