የተመ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዘገባና ኤርትራዉያን ተቃዉሞ
ሰኞ፣ ሰኔ 15 2007ማስታወቂያ
የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኤርትራ መጠነ ሰፊ ቁጥጥርና የጭካኔ ርምጃ ሰበብ ወደ 360 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ወደ አዉሮጳ እንዲሰደዱ መዳረጋቸዉን አስታዉቆ ነበር ። ዛሬ ጄኔቭ ላይ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዉያን በተቃዉሞ ሰልፉ ላይ እንደተገኙ የገለፁልን አቶ ሲራክ ባህልቢ፤ ክሱ የኤርትራን ሥም ለማጉደፍ የታለመ ፖለቲካዊ ይዘት ያለዉ ባዶ ክስ ነው ሲሉ አስተባብለዋል፤ አቶ ሲራክ በሰልፉ ላይ እንዳሉ በስልክ አነጋግሪያቸው ነበር ። የተቃዉሞ ሰልፉ መልዕክት ምን እንደሆነ በማብራራት ይጀምራሉ ።
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ