የተመ ድርጅት ስለ ዩክሬን ጦርነት ማን ማድረግ ይቻለዋል?
ሰኞ፣ የካቲት 21 2014
ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በሩሲያ የዩክሬን ወረራ ላይ ለመወያየት ዛሬ ይሰበሰባል። ጉዳዩ ወደ ጠቅላላ ጉባኤው የተመራው በጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ሲሆን የሩሲያን ወረራ ለማውገዝ የተዘጋጀ የውሳኔ ሐሳብ ይቀርብለታል። ጠቅላላ ጉባኤው አስቸኳይ ስብሰባ ሲያደርግ በ40 አመታት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም በዩክሬን ጥያቄ በጉዳዩ ሊወያይ ዝግጅት ላይ ነው።
ዩክሬን የአውሮፓ ኅብረትም ሆነ የኔቶ አባል ባትሆንም ከኅብረቱ አባል አገራት በተናጠል እና በጋራ ድጋፍ እያገኘች ትገኛለች። የሩሲያ ወረራ ከዚህ ቀደም ገለልተኛ የሚባሉ እንደ ስዊትዘርላድ ያሉ አገሮችን ጭምር ለዩክሬን እንዲያግዙ አስገድዷል። የአውሮፓ አገራት በርከት ያሉ ማዕቀቦች በሩሲያ፣ በባለሥልጣኖቿ እና በተቋማቷ ላይ እየጣሉ ነው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለዩክሬን ምን ማድረግ ይቻለዋል? የአውሮፓ አገራት ለሩሲያ ወረራ በተናጠል እና በኅብረት የሰጧቸው ምላሾች ምን ፈየዱ? የብረስልሱ ወኪላችንን አነጋግረነዋል።
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሰ