የተራዘመዉ «ለወገኔ እሮጣለሁ» ሩጫ በኦሮሚያ
ማክሰኞ፣ ጥር 8 2010ዉድድሩ በፀጥታ ምክንያት በስምንት ከተሞች እንዳይካሔድ የሐገርቱ የደህንነት መስሪያ በት በመጠየቁ የአዘጋጆች ኮሚቴ አባላት በጥያቄዉ ላይ እየተወያዩ በመሆናቸዉ ለመራዘሙ ምክንያት መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ማስታወቃቸዉን ዘግበን ነበር።
አሁን የዉድድሩ ዝግጅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፣ ምን ያህል ገቢ እንደተሰበሰበ የኮሚቴዉ አባል የሆኑት አቶ ገመዳ ኦልአና ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።
በጤና ምክንያት መሮጥ ከማይችሉት ዉጭ ፆታ እና እድሜን ሳይለይ አዲስ አበባን ጨምሮ በ20 የኦሮሚያ ዞኖች 150ሺ ሰዎችን በዉድድሩ ለማሳተፍ ዕቅድ እንዳላቸዉ የአሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሐላፊ እና የኮሚቴዉ ሰብሳቢ አቶ ሞቱማ ተመስገን ለይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ከተሳታፍዎቹ ዉስጥ ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌት ኢብራህም ጄይላን፣ አትሌት ስለሺ ስህን፣ አትሌት ገንዘቤና አትሌት ጥሩኔሽ ዲባባን ጨምሮ ሌሎችም እንደሚሳተፉ ገልፀዋል።
ሩጫዉ በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ክልሎች ለማኪያሔድ ዝግጅት ኢያደረጉ እንደሚገኙ አቶ ሞቱማ ይናገራሉ።
ይሁን እንጂ ሩጫዉ እንዲካሄድ ከታቀደባቸዉ 22 ከተሞች ዉስጥ ቢያንስ ስምንት በሚሆኑት ከተሞች ላይ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ውድድሩ ይካሄድ፤ አይካሄድ በሚለዉ ጉዳይ ኮሚቴዉ እና የፀጥታ አካላት ዉይይት በማድረግ ላይ እንደነበሩ ከዉስጥ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አቶ ሞቱማ ግን የደረሰን ጥያቄ የለም ይላሉ።
ገንዘቡ ከተሰበሰበ በኋላ የተፈናቀሉትን ለመርዳት ለተቋቋመ ለሌላ ኮሚቴ እንደሚሰጥም አቶ ገመዳ አክሎዉ ገልፀዋል።
መርጋ ዮናስ
ነጋሽ መሐመድ