የተሻለ የደን ይዞታ ያስፈልጋል20 ሐምሌ 2002ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2002የዓለም የምግብና ግብርና ድርጅት በአዉሮጳዉያኑ 2007ዓ,ም ይፋ ባደረገዉ ዘገባ ኢትዮጵያ የደን ይዞታቸዉ እየተመናመነ ከሚገኙ አገራት ከመጨረሻ በአምስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል picture alliance/imagestate/Impact Photosማስታወቂያበዚህ ዘገባ መሠረት ኢትዮጵያ የቀደመቻቸዉ አገራት ከሰሃራ በረሃ ዳር ላይ የሚገኙትና ተፅዕኖዉ የሚያጠቃቸዉ እንደነማሊ፤ ኒዠርና ሞሪታንያ የመሳሰሉት አገራት ናቸዉ። ጥናቶች በተደጋጋሚ እንዳመለከቱትም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የደን ይዞታቸዉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ አገራት ከጥቂት አስርት ዓመታት በኋላ የደን ሃብታቸዉ ጨርሶ ሊጠፋ ይችላል የሚል ነዉ። ሸዋዬ ለገሠ፤ ሂሩት መለሠ