የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የኢድ አል አደሃ በዓል መልዕክት
ቅዳሜ፣ ሐምሌ 10 2013
ማስታወቂያ
የመስዋዕትነት በዓል በሚል የሚጠራው የ ኢድ አል አደሃ ዓረፋ በዓል በእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በመጪው ማክሰኛ በልዩ ልዩ ሥነ ሥርዓቶች ይከበራል።
በዓሉን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ኢትዮጵያውያን ወደ አንድነት እንዲመጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዓሉ በሰላምና በመረዳዳት እንዲከበር የጠየቁት ተቀዳሚ ሙፍቱ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በብሔረሰብ መለያየት መወገዝ አለበት ብለዋል።
ጦርነት፣ አመፅ አይጠቅምም ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ወደ ሰላምና አንድነት እንመለስ አገራችንንም ከማጥፋት እንቆጠብ በማለት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥሪ አቅርበዋል።
ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ