1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፤ የተቃዋሚዎችና የገዥዉ ፓርቲ ድርድር

እሑድ፣ ጥር 21 2009

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች እና የገዥዉ ፓርቲ ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተዉ ተወያይተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃዉሞ እና የአደባባይ ሰልፍ ከገጠመዉ ወዲህ ተቃዉሞዉን ለማርገብ ከወሰዳቸዉ ርምጃዎች አንዱ ሃገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መወያየት የሚለዉ ነዉ።

Äthiopien Epiphanie in Addis Abeba
ምስል Thomas Haile

ውይይት፦የተቃዋሚዎችና የገዥዉ ፓርቲ ድርድር

This browser does not support the audio element.


በቅርቡ የተደረገዉ የተቃዋሚዎችና የገዥዉ ፓርቲ ዉይይትም በዚሁ በመንግስት እቅድ ላይ የተመሰረተ ነዉ። ዉይይቱ የመነጋገርያ አጀንዳ ለመቅረጽ እና ሃሳቦችን ለመለዋወጥ የተደረገ መሆኑ ከመነገሩ ዉጭ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች እንዳልተነሱበት ተሳታፊዎች ይናገራሉ። አንዳንድ ታዛቢዎች ዉይይቱ ለወደፊቱ ተቃዋሚዎችን ከገዥዉ ፓርቲ ጋር ለማቀራረብ ይጠቅማል ይላሉ። የዛኑ ያክል ዉይይቱን በርካታ ተቃዋሚዎች በተለይም መቀመጫቸዉን ከኢትዮጵያ ዉጭ ያደረጉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ያገለለ በመሆኑ ሁሉን አካታች አይደለም ሲሉ ትችት የሚያሰሙ አሉ። በሌላ በኩል መንግሥት በዉይይቱ የሥነ-ምግባር ደንብ ካልፈረሙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ጭምር እንደሚወያይ ገልጾአል። ይህ ዝግጅታችን የተቃዋሚዎችና የገዥዉ ፓርቲ ዉይይት ያስነሳዉ ክርክርና ፖለቲካዊ ፋይዳዉን ያስቃኛል።  በዉይይቱ ላይ የተሳተፉት ዶ/ር ጫኔ ከበደ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዎ ፓርቲ «ኢዴፓ» ፕሬዚዳንት ፤ አቶ ሙሉጌታ አበበ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት «መኢአድ» ሃላፊነት ምክትል ፕሬዚዳንት፤ ዶ/ር ተሾመ ታፈሰ የአመራርና አስተዳደር ተቋም መምህር፤ እንዲሁም አቶ ዩሱፍ ያሲን የፖለቲካ ተንታኝ ናቸዉ። ሙሉ ዉይይቱን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

     
አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW