1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተካረረው የሩሲያ እና የአውሮፓ ኅብረት ውዝግብ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 12 2013

ሩሲያ እና የአውሮፓ ኅብረት እንደገና እየተወዛገቡ ነው። የአሌክሲ ናቫልኒ ጤንነት እና በቼክ ሪፐብሊክ እና በሩሲያ መካከል የተቀሰቀሰው ውዝግብ ከገፊ ምክንያቶቹ መካከል ይገኙበታል። ሩሲያ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ወታደሮች ማከማቸት መጀመሯ ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል አስጠንቅቀዋል።

TABLEAU | Russland Maslovka | Konflikt in der Ostukraine | Panzer
ምስል REUTERS

የተካረረው የሩሲያ እና የአውሮፓ ኅብረት ውዝግብ

This browser does not support the audio element.

የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ሩሲያ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ የጀመረችው ወታደራዊ ዝግጅት ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል በትናንትናው ዕለት አስጠንቅቀዋል። ኃላፊው ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የመስክ ሆስፒታሎችን ጨምሮ "ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያዎች" ሩሲያ ከዩክሬን በምትዋሰንበት የክሬሚያ አካባቢ እያከማቸች ነው። 

በምሥራቃዊ ዩክሬን በሩሲያ የሚደገፉ ተገንጣዮች እና የዩክሬን መንግሥት ኃይሎች መካከል ለሰባት አመታት በተደረገ ውጊያ ከ14,000 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ውጊያው የተቀሰቀሰው ሩሲያ ክሬሚያ የተባለችውን ግዛት በኃይል ከዩክሬን ከገነጠለች በኋላ ነው። የአውሮፓ ኅብረት የሩሲያን ድርጊት ቢቃወምም በተግባር ግን ምንም ያመጣው ለውጥ አልነበረም። 

ከዚህ በተጨማሪ በሩሲያ እና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል የተቀሰቀሰው ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ እና በእስር ላይ የሚገኘው አሌክሲ ናቫልኒ ጤንነት በዚህ ሳምንት ተጨማሪ የውዝግብ መነሾ ሆነዋል። በአሌክሲ ናቫልኒ ጤንነት እና ደሕንነት ጉዳይ 27 አባል አገራት ያሉት የአውሮፓ ኅብረት የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጽህፈት ቤት ተጠያቂ እንደሚያደርግ ጆሴፍ ቦሬል ገልጸዋል። 
በዛሬው የአውሮፓ እና ጀርመን መሰናዶ ገበያው ንጉሴ የተካረረውን የሩሲያ እና የአውሮፓ ኅብረት ውዝግብ ይቃኛል። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

ገበያው ንጉሴ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW