1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተወሳሰበው የኢትዮጵያ ፖለቲካ መንስኤና መፍትሄው

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 2 2015

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፖለቲከኛ መረራ ጉዲና እንደሚሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስብስብ ባህሪ በአንድ ጀንበር ያልተፈጠረ እንዳለመሆኑ በአንድ ጀንበርም አይፈታም፡፡ ፕሮፌሰር መረራ ታሟል ያሉትን የአገሪቱ ፖለቲካ ሳያክሙ በኢትዮጵያ የሰፋውን ችግር ማርገብ አይቻልም ሲሉም ነው አስተያየታቸውን የሰጡት።

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር የሚያደርጉት ዉይይት
የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር የሚያደርጉት ዉይይትምስል Solomon Muchie/DW

 

 

የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙ ፖለቲከኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ «እየተወሳሰበ ነዉ» ያሉትን የሐገሪቱን ፖለቲካዊ ችግር ለማቃለል የረጅም ጊዜና የጋራ ጥረት እንደሚያስፈልግ አስታወቁ።

ፖለቲከኞቹ እንደሚሉት በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖረዉ ህዝብ የሚያነሳዉ ጥያቄ ደረጃዉ ቢለያይም መሰረታዊ ልዩነት የላቸዉም። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሥዩም ጌቱ ያነጋገራቸዉ ሁለት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንደሚሉት የህዝብን ጥያቄዎችንም ሆነ ልዩነቶችን ለመፍታት የሰከነ ዉይይት ያስፈልጋል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፖለቲከኛ መረራ ጉዲና እንደሚሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስብስብ ባህሪ በአንድ ጀንበር ያልተፈጠረ እንዳለመሆኑ በአንድ ጀንበርም አይፈታም፡፡ ፕሮፌሰር መረራ ታሟል ያሉትን የአገሪቱ ፖለቲካ ሳያክሙ በኢትዮጵያ የሰፋውን ችግር ማርገብ አይቻልም ሲሉም ነው አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡

“ወዴትም አቅጣጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ብንሄድ የህዝቡ ጥያቄ ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ አብዛኛው ህዝብ የተሸለ ኑሮ መግፋት ነው ፍላጎቱ፡፡ ሊዕቃን የሚባሉቱ ግን ጥያቄ ብለው የሚያነሱት የሚጋጭ ህልም ለው ነው፡፡ ወደ አማራው ብትሄድ ሊዕቃኑ የድሮ ኢትዮጵያ ካልተመለሰች ሲሉ እንደ ኦሮሞ ሊዕቃን ያሉ ግን ያቺን ኢትዮጵያ እንደ ብሔሮች እስር ቤት መለከተዋል፡፡ ህልሞቹ የሚጋጩ ከሆነ ደግሞ መፍትሄውም ቀላል አይሆንም” ሲሉ የአገሪቱ ችግሮች ውስብስብ ባህሪን በአተያየታቸው አብራርተዋል፡፡ዉይይት፤ብሔራዊ ምክክር የኢትዮጵያን ቀዉስ ለማቃለል ይረዳ ይሆን?

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፖለቲከኛ መረራ ጉዲና እንደሚሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስብስብ ባህሪ በአንድ ጀንበር ያልተፈጠረ እንዳለመሆኑ በአንድ ጀንበርም አይፈታም፡፡ ፎቶ፤ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበርምስል DW/Yohannes G. Egziabher

ከአምስት ዓመታት በፊት በአገሪቱ የተመሰረተው የመንግስት ለውጥ በወቅቱ በርካቶችን አስፈንጥዟል፡፡ ያ በመልካምነቱ ጎልቶ የተነሳው የፖለቲካ ለውጡ እምብዛም ሳይዘልቅ ተቃውሞና ነቀፌታው በዝቶበት ተስተዋለ፡፡ ለሌላኛው አስተያየት ሰጪ ፖለቲከኛ የቀድሞ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ ተስተጓጎለ ያሉት  የለውጥ ሂደቱ አሁን ላይ አገሪቱ ለገባችበት ቀውስ አብይ ምክኒያት ነው፡፡ “ለኔ አሁን ለምናስተውለው መሰረታዊው የዚህ አገር ችግር በሊዕቃን የብሔርተኝነት እና የአሃዳዊነት ፍረጃ አይመስለኝም፡፡ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው መንግስታዊ ለውጥ እውነተኛ በሆነ መንገድ ባለመተግበሩ በያከባቢው እምነት ማጣቱና በሚፈለግ ደረጃ የህዝብ ትያቄ አለመመለሱ መስለኛል” ሲሉም አስተያየታቸውን አብራርተዋልአረና ትግራይ የፕሪቶሪያ ስምምነት በአስቸኳይ ይተግበር አለ

የአዲስ አበባ ከተማ በከፊልምስል Solomon Muchie/DW

መንግስታዊ ለውጡ የቱጋ ይሆን ከበዛው ድጋፍ ከፍ ላለው ተቃውሞ እንዲጋለጥ ምክኒያት የሆነው ክስተት የተፈጠረው የተባሉት ፕሮፌሰር መረራ በፊናቸው ለፖለቲካው ቀውስ ዋናው ምክኒያት የፍላጎቶች መጣረዝ ነው ይላሉ፡፡ “በወቅቱ እኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚናገሩዋቸውን ቃል እንዲጠብቁ ደግሞም የሚደግፋቸውን ብቻ ሳይሆን የሚነቅፉአቸውንም እንዲሰሙ መክሬያቸዋለሁ፡፡ እናም ትልቁ ችግር የሁሉንም ኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ማዕከል አድርጎ መጓዝ ላይ ነው” ብለዋል፡፡ እንደ ፖለቲከኛው አስተያየት የሚጓተተው የሊዕቃን ፍላጎት እና የሁሉም ህዝብ ጥያቄ ማቻቻል ላይ ክፍተት መፈጠሩ አሁን ለሚስተዋለው ለመፍታትም ቀላል ላልሆነው የፖለቲካ ሁኔታ መር ከፍቷል፡፡የሁለት ጉምቱ ፖለቲከኞች ስደት አንድምታ

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የቆየው የትግራይ ክልል ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት ገጥሞት ከጦርነት ማግስት ወደ መደበኛ ኑሮ ለመመለስ የሚደረግ ጥረት ላይ ነው፡፡ ይሁንና በዚህም ክልል ፖለቲካዊ ጥያቄዎቹ ገና መቋጫ ማግኘታቸው ቀሪ ስራ ይጠይቃል፡፡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችም የየራሳቸው መልክ ያላቸው ግጭቶች በየክልሎቹ የሚገኙትን ማህበረሰብ ለከፋ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተግዳሮቶች መዳረጋቸውን እንደቀጠለ አለ፡፡ አስተያየት ሰጪ ፖለቲከኞቹ ግን ለሁሉም ችግሮች ተቀምጦ ከመወያየት ሌላ መውጫ መንገድ የለም ይላሉ፡፡ “ይህ ሁሉ ችግር በአንድ ፓርቲ ብቻ ሊፈታ የሚችል አይደለም፡፡ ሸክሙም ቀላል አይሆንለትም፡፡ በመሆኑም ከመገዳደል ወጥተን ወደ መደራደር ፖለቲካ መጥተን የአገሪቱን ፖለቲካ መሰረታዊ በሆነ መንገድ መፍታት አለብን” ብለዋል ፖለቲከኛ መረራ ጉዲና፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት  በተለያዩ አከባቢዎች ለሚስተዋሉ ግጭቶች የሰላም አማራጭን ከማቅረብ እንደማይቦዝንና አስገዳጅ ከሆኑ ብቻ ወደ ጦርነት ለመግባት እንደሚገደድ ደጋግሞ ያነሳል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW