1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ

ሰኞ፣ ነሐሴ 8 2015

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሳምንት በፊት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ ዛሬ አጸደቀ። አዋጁን 16 የፓርላማ አባላት ሲቃወሙት፤ 12 አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል። በአማራ ክልልና "እንዳስፈላጊነቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች" ተግባራዊ እየተደረገ ለሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ተሰይሟል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል። ምስል Ethiopian Press Agency

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተቃወሙት ሁሉም የፓርላማ አባላት ከአማራ ክልል ተመርጠው በተወካዮች ምክር ቤት የገቡ ናቸው።

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሳምንት በፊት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ ዛሬ አጸደቀ። አዋጁን 16 የፓርላማ አባላት ሲቃወሙት፤12 አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28፤ 2015 ዓ.ም በሙሉ ድምጽ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት፤ በአማራ ክልል እና “እንዳስፈላጊነቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች” ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማጽደቅ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተገኙት አባላት ከፍተኛ ክርክር እና በርካታ ነጥቦችን ማንሳታቸዉ ተመልክቷል

ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ብቻ እንዲወሰን ለመንግስት ጥሪ አቀረበ

አዋጁ የተደነገገው "በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የሕግ ማስክበር ሥርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ" እንደሆነ መንግሥት ማስታወቁ ይታወቃል

እስራኤል ከ200 በላይ የሚሆኑ ዜጎቿን ከአማራ ክልል አወጣች

ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ሰባት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላትን በመሰየም አፅድቋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላቱ፤አቶ አዝመራው አንዴሞ ሰብሳቢ፤ ወ/ሮ ነጃት ግርማ ዶ/ር ምክትል ሰብሳቢ፤ አቶ ሣዲቅ አደም አባል፤ አቶ መስፍን እርካቤ አባል፤ ዶ/ር አብርሃም በርታ አባል

ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተሰየሙት የመርማሪ ቦርድ አባላት በጉባዔው ፊት ቃለ መሀላ መፈጽመዋል ምስል Ethiopian Press Agency

ወ/ሮ ፍሬህይወት ተሾመ አባል፤ አቶ ወንድሙ ግዛው ናቸዉ። ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተሰየሙት የመርማሪ ቦርድ አባላት በጉባዔው ፊት ቃለ ማህላ መፈጸማቸውም ታዉቋል።

 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW