1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተዘጋዉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት በኢትዮጵያ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 19 2015

የኢንተርኔት አገልግሎት የሚያገኙ ሁሉ ያሻቸውን በማኅበራዊ ድረ ገፆች ማሠራጨት በሚችሉበት በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲህ አይነቱን ዕድል ገድቧል። በኢትዮጵያ ቲክ ቶክ፣ ኢንስታግራም ወይም ዩቲዩብ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን የተከለከሉት የተቃዋሚ አባላት ብቻ አይደሉም።

Symbolbild I BigTech I Social Media
ምስል Ozan Kose/AFP/Getty Images

የተዘጋዉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት በኢትዮጵያ

This browser does not support the audio element.

አናናሱን ነጋዴው በእጁ በያዘው ቢላ በመልክ በመልኩ አጽድቶ ይቆርጣል፡፡ ሁለት የፊልም ተማሪዎች የነጋዴውን ሥራ ከሁሉም አቅጣጫ መቅረጽ ጀምረዋል፡፡
ልጆቹ ቪዲዮን በዩቲዩብ ወደፊት ለቀው ሓብታምም ፣ተዋቂም መሆን አይችሉም፡፡ ምክንያቱም መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት መስመሩን - ማንም እንዳይጠቀም ወኪላችን እንደአለው እዚያ ዘግቶታል፡፡ከተዘጋም ሰንበት ብሎአል፡፡

አንደኛው ተማሪ ግዛው ብርሃኑ እሱ ለጣቢያችን ለ ዲ ደብልዩ እንደአለው ብዙ ነገሮችን ሰብስቦ ማቅረብ ሙያው ስለሆነ ይችልበታል፡፡ ነገር ግን የኢንተርኔት መስመሩ በመዘጋቱ የስራውን ድካም ለተመልካቾች ለማቅረብ ያለው ዕድል  እሱ እንደአለው "ውስን ነው፡፡" 

ይልቅስ ቪፒኤን የሚባለውን መስመር መጠቀም ይቻላል፡፡ አሱን መስመር የሚያውቁትና አሱን የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ትንሽ ነው፡፡

ለብዙዎቹ ቪፒኤን ከዚያ እንደ ተሰማው በአንድ በኩል ስለሚከፈልበት ውድ ነው፡፡ በሌላ በኩል እሱን መጠቀም ደግሞ ለተራው ሰው አስቸጋሪና ውስብሰብ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እገዳውን የጣለበትን ምክንያት ሲያስረዳ "የሐሰት ዜናዎች በአገሪቱ እንዳይስፋፋ ለማገድና ለመቆጣጠር ነው" ይላል፡፡

ይህን ለማድረግ ግን አቶ በፈቃዱ ኃይሉ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት ማዕከል ተጠሪ ለጣቢያችን ሰሞኑን እንደአሉት መንግሥት እንደዚህ ዓይነቱን እርምጃ ለመውሰድና ለማገድ ሕጋዊ የሆነ መብት እንደሌለው እሳቸው እግረ መንገዳቸውን አንስተዋል፡፡  

ካሮሊን ኢምሉ/ይልማ ኃይለሚካኤል

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW