የተገፋው የአውሮጳ ሕብረት ልዩ ጉባኤ
ሰኞ፣ መስከረም 18 2013ማስታወቂያ
የአውሮጳ ሕብረት አስቸኳይ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እና ዓርብ ሊያካሂድ አቅዶ የተስተጓጎለው ጉባኤ በዚህ ሣምንት እንደሚካሄድ ይጠበቃል። ያለፈው ሳምንት ስብሰባ የተሰረዘው የሕብረቱ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርልስ ሚሸል ከቅርብ ሰዎቻቸውን አንዱ በኮቪድ 19 መያዙ በምርመራ ሲረጋገጥ ሚሼል ራሳቸውን አግልለው ማቆየት በመገደዳቸው ነው። የምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ከተደረገላቸው ተደጋጋሚ ምርመራ በኋላ ከተሐዋሲው ነፃ መሆናቸው በመረጋገጡ ሕብረቱ ወሳኝ አጀንዳዎቹ ላይ ተነጋግሮ ውሳኔ ለማሳለፍ በያዝነው ሳምንት ሐሙስ እና ዓርብ ልዩ ጉባኤውን ያካሂዳል ተብሏል። በጉዳዩ ላይ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤን ስቱዲዮ ከመግባኤ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ገበያው ንጉሤን
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ