የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብት በወንጀል ምርመራ ወቅት
ሰኞ፣ ግንቦት 30 2013ማስታወቂያ
በወንጀል ምርመራ ወቅት የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ላይ መሻሻሎች መምጣታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገለጸ። ቢሮው ዘርፉን ለማዘመን እና ሕጋዊ አሠራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ያግዘኛል ያለውን በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ የከፈተውን ማዕከልም በይፋ አስተዋውቋል። ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ እንዲያዙና ምንም አይነት ሰብዓዊ ጥሰቶች ሳይፈጸምባቸው ለፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለማስቻልም የባለሙያዎች የሙያ ክህሎት ላይ በአዲስ መልክ እየተሠራ መሆኑም ነው የተነገረው።
ስዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ